Kiya wondifraw

Kiya wondifraw

Share

እንደመሸ አይቀርም

28/01/2023

?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ለስጋው ባደላ ምድራዊ ሽንገላ
ሚዛናዊ ፍትህ ዐይኗን ተከልላ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ማጥ በዋጠው ጭቃ እሾህ ተደብቆ
ቅርብ ያለ እንዳይታይ ማስተዋል እርቆ
አፍ ባዳጠው ምላስ ላንቃ ተሰንጥቆ
በአንገት ሲቆም ራስ ቅባት ተለቅልቆ
ደም ያጋተ መስቀል ቁልቁል ተዘቅዝቆ
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ባይችል አይሰጥ ጫንቃ ሸኽሙ እየከበደ
ቅን ያቀናው መቅደስ ሰርክ እየተናደ
ያዳቆነ ሰይጣን ቄስ አንደ አለመደ
ታሟል ያልነው ሳይድን ጤነኛ ካበደ
ዛሬም አንደ አህዛብ ጳጳስ ፍቅርን ካደ ?
፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡፡
ኪያ ወንድይፍራው ካሳ
(WKW)

02/03/2022
13/01/2022

የብርሀን አክሊል የሌት ቀንዲል ሻማ
የተስፋ ጎህ ብስራት ፋና ወጊ ግርማ
ከሚያወዛውዛት- ንፋስ መሐል ቆማ
እንባዋን ስታፈስ--ድምጿን ሳታሰማ
በጥቁር ቀን ስቃ ምሽቴን አድምቃ
ብርሀን ሆና ለዐይኔ ፅልመቴን ደብቃ
ማልዶ ልጠይቃት ከእንቅልፌ ስነቃ
የእልም ዐለም ቅዠቴን የሌሊቱን ሲቃ
አብራች መች አደረች ቃልኪዳን ጠብቃ
ደእቃ አየኋት ጠዋት ከመሬት ተጣብቃ

13/11/2021

በጥቁር ደመና ሰማይ ተከልሎ
ጥላ እንዳይራመድ ዳናን ተከትሎ
ቀኑም አኮረፈ ጭጋግ ፊቱን ጥሎ.......
በኢትዮጵያ ሰማይ ስር መሬት ባለው እውነት
የእብሪት ሀይሎች ሴራ ክፋት ምቀኝነት
በዘር ደዌው...... ቁስል ነቀርሳ ስውነት
እኩያን ተጋርጠው ገጥመዋል ጦርነት.......
እርግጥ ነው አምላኬ የትውልድ ካአንተ እርቋል
ቃል ኪዳኑን ሽሮ የዲያብሎስን መርጧል
በቅዱሳን ምድር ስለት አንገት ቆርጧል
ነፍስ እየቃተተች ሰው እንደ በግ ታርዷል......
የጭካኔ አጥር ጥግ የክፋት ዳርቻ
የገነት በር ቁልፍ ሲጠፋ መክፈቻ
በወዳጅ ባላንጣ ይፈርሳል ጉልቻ.......
ሰይጣን ኩሎ ሲድር ባልንጀሩን ጠርቶ
አባት ልጁን ደፍሯል ክብሩን አጠልሽቶ........
ማጣፊያው ካጠረ በሰማኒያው ባሌ
የግፍ እጅ ረዝሞ በአርባው ቀን እድሌ
ከስብ ስም ይሸታል በእሳት ሳይግል ገሌ.......
የከረመ ውሀ እና የእናት ሆድ አይከፋ
ብለው ተረቱ አሉ ከአፍ ምራቅ ሲጠፋ

Category

Telephone

Website

Address

Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Kiya wondifraw posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.