Ethio beauty's

Ethio beauty's

Share

VOICE OF ETHIOPIA /VOE / politics. religions, social. economic, sport.

Photos from Ethio beauty's post 05/10/2026

25/01/19
እንኳን ለዳግም ምርጫ አበቃዎት የሚል የደስታ መግለጫ
ሀገራችን ኢትዮጵያ በታሪኳ አዲስ ምዕራፍ በሚከፍት መልኩ በጀመረችው የታላቅነትና የብልጽግና ጉዞ ላይ፣ ሀገርን በመምራትና ህዝብን በማገልገል ዳግመኛ የጠቅላይ ሚኒስትርነት ኃላፊነት ተሰጥቶዎት በመመረጥዎ የተሰማኝን ወሰን የሌለው ደስታና ኩራት በታላቅ አክብሮት እገልጻለሁ።
ላለፉት ዓመታት ለሀገር ሰላም፣ ለልማት፣ ለኢኮኖሚ እድገትና ለሀገራዊ አንድነት ያሳዩት ቁርጠኝነት፣ አርቆ አስተዋይነትና የማይናወጥ የአመራር ብቃት የብዙዎቻችንን ልብ ማረከ ከመሆኑም በላይ ለሀገራችን ተስፋንና ብርሃንን ፈንጥቋል። የወሰዷቸው አቅጣጫዎችና ያስመዘገቧቸው ስኬቶች ለኢትዮጵያ ታላቅነት ያለዎትን ቀናኢነትና ፍቅር በግልጽ የሚያሳዩ ናቸው።
በመሆኑም አምላክ ለዚህ ታላቅ የአገልግሎት ኃላፊነት ዳግመኛ ስላበቃዎት እንኳን ደስ አለዎት!
በቀጣይም ሀገራችንን ወደ ተሻለና ወደታላቅ የስኬት ማዕረግ በሚያሸጋገሩት የልማትና የሰላም ጉዞ ላይ ሙሉ ጥንካሬውን፣ ጥበቡንና ጤናውን ይሰጥዎ ዘንድ እመኛለሁ። ከጎንዎ ሆነን ለሀገራችን እድገት ለማበርከትና ራዕይዎ እንዲሳካ ድጋፋችን አይለይም።
ለእርስዎና ለቤተሰብዎ ሙሉ ጤናን፣ ለሀገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ሰላምን፣ ፍቅርንና ብልጽግናን እመኛለሁ!
ኢትዮጵያ በክብርና በታላቅነት ለዘላለም ትኑር!
ከታላቅ አክብሮትና ፍቅር ጋር፣
አክበሪዎት ነብይ ፍፁም ሱልጣን

05/10/2026

My pm Abiy Ahmed Ali💪💪💪

26/08/2026

ሁሉም የደርስ

25/08/2026

ዘላለም መንግሥቱ ለተበለ የቤተ ክርስቲያንን ጣለት የተሰጠ መልስ፦ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ለማፍረስ የሚደረግ የተቀናጀ ዘመቻ
የእግዚአብሔርን ህዝብና የቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ሥርዓት ባለው መልኩ ለመምራት የተቋቋመውን የኢትዮጵያ ወንጌል አማኞች አብያተ ክርስቲያናት ካውንስል እና የመሪዎቹን ስም ለማጥፋት አቶ ዘላለም መንግሥቱ የጻፈው ጽሑፍ፣ እውነትን የመፈለግ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያንን አንድነት የመሸርሸር አላማ ያለው መሆኑን መገንዘብ ያስፈልጋል።
1. የታሪክዊ ጣለቶችን እና የውስጥ ጠላቶች አጀንዳን ማስፈጸም
* የአንድነት ጠላት፦ የወንጌል አማኞች ካውንስል ከተቋቋመ ጀምሮ በአገራችን ያሉትን የተለያዩ አብያተ ክርስቲያናት በማስተባበርና አንድነታቸውን በማጠናከር ላይ ይገኛል። ይህንን አንድነት መስበር የሚፈልጉ የአገርና የቤተ ክርስቲያን ታሪካዊ ጠላቶች፣ በቃላት ጨዋታና በጽሑፍ ስም በማጥፋት ሕዝቡን ለመከፋፈል አቶ ዘላለምን እንደ መሣሪያ በመጠቀም ላይ ናቸው።
* ጥላቻን መዝራት፦ ጽሑፉ የቤተ ክርስቲያንን መሪዎችን የካውንክሉን መሪዎች ስም በAi በተቀናጀ ሲስተም ያለ ምንም ሕጋዊ ማስረጃና መረጃ በውሽት"በላተኞች"፣ "ወንጀለኞች" እና "ጉቦኞች" እያለ በመፈረጅ፣ በአማኙ ሕዝብ ዘንድ ጥርጣሬንና መከፋፈልን ለመፍጠር የተዘጋጀ መርዝ ነው።
2. በቴክኖሎጂ (AI) የታገዘ የሐሰት ማስረጃ እና ስም የማጥፋት ደባ
* የAI አጠቃቀምና እውነታው፦ ጸሐፊው በጽሑፉ ማጠቃለያ ላይ “የብሩን ምስል የሠራሁት በAi ነው” በማለት በገዛ እጁ እንደተናገረው፣ የያዘው ማስረጃ በሙሉ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) የተቀናበረና የሐሰት ሰነድ ነው።
* የተፈበረከ ውንጀላ፦ በምናባዊ ቴክኖሎጂ ማስረጃ እየፈበረኩ የመሪዎችን ስም ማጥፍት :የጸሐፊውን ተዓማኒነት ዜሮ: የሚያወርደው ከመሆኑም በላይ፣ አላማው እውነትን ማውጣት ሳይሆን በሐሰት ስም ማጥፋት (character assassination) የገንዘብና የጥቅም መገኛ መንገድ ማድረጉን ያሳያል። እንድህ የለ ነገር ደግሞ ወንጀል ነው ።
3. የከውንስሉን መሪዎች በመስደብ የሚደረግ የገንዘብ ንግድ
* ስም በማጥፋት መጠቀም፦ አቶ ዘላለም በካውንስሉ መሪዎችና ተቋማት ላይ የከፈተው ዘመቻ ግላዊ ጥላቻንና ከጀርባ ያሉ አካላትን ፍላጎት በማስፈጸም የገንዘብ ጥቅም ለማግኘት የተደረገ ነው።
* የበግ ቁርበት የለበሰ ውፌታ፦ በጽሑፉ መግቢያ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችንና የታዋቂ ሰዎችን አባባል በመጥቀስ መንፈሳዊ ለመምሰል ቢሞክርም፣ የጽሑፉ ዋና ፍሬ ግን ስድብ፣ ሐሜት፣ ግላዊ ጥቃትና የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር የማፍረስ ፍላጎት አጀንዳ መኖሩ ያስታውቃል ።
ማጠቃለያ
የወንጌል አማኙ ሕዝብና የአብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እንዲህ ያሉ በAI የታገዙ የሐሰት ውንጀላዎችንና የከፋፋዮችን ሴራ በንቃት ሊረዱት ይገባል። ካውንስሉ የተቋቋመበትን ታላቅ ዓላማ በመጠበቅ፣ በሐሰት ወሬና ስም በማጥፋት የገንዘብ ጥቅም የሚያደናግሩ አካላትን አጋልጦ ማውጣትና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት መቆም የሁላችንም ኃላፊነት ነው። አቶ ዘላለም ሚስታቸውን ፈተው የሚስታቸውን ሚዜ አግብተው የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቀው አሜሪካ አገር እንደሚኖሩ ይታወቃል እና ምነው የእሳቸው የትዳር ጉዳይ ከሁሉ አይበልጥም በምን ሞራል ነው መጽሐፍ ቅዱስን የሚጠቅሱት ደግሞም አዚሁ አገር ውስጥ ሆናችሁ ከአመንዝራው ዘላለም ጋር የገጠማችሁ ምንደኞች ስለምትታወቁ እንነጋገራለን ።

Telephone

Website

Address

Omedla Streat
Addis Ababa

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethio beauty's posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.