Ethiopian for African

Ethiopian for African

Share

INTERNATIONAL MINDS

18/10/2026

ሰላም ማረጋገጥ የጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊታችን የማይቀለበስ ቃል ኪዳን ነው

ሠራዊታችን የሀገርን ዳር ድንበር ለማስከበር እያደረገ ላለው ታላቅ ተጋድሎ እና ሕግ የማስከበር አመርቂ ውጤቶች ያለውን ሙሉ ድጋፍ ከህዝብ አገኝቷል። የኅብረ ብሔራዊ ወንድማማችነት እና እኅታማችነት አርማ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊታችንን እንደግፋለን! የመከላከያ ሠራዊታችን፣ የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎቻችን ለሀገር ሰላም እና ሕልውና የከፈሉት መሥዋዕትነት ሁልጊዜም በወርቃማ ታሪካችን ውስጥ ከፍ ያለ ክብር የሚሰጠው ነው።

የእስካሁኑ ድል የሀገራችንን የወደፊት ብሩህ ተስፋ እና የማይታጠፍ ራዕይ ግልጽ አድርገው ያሳዩ ናቸው። “ከግድቡ ወደ ወደቡ እንሸጋገራለን! የባሕር በር ባለቤትነታችን በልጆቿ መሥዋዕትነት እውን ይሆናል!” በሚሉ መፈክሮች የኢትዮጵያ ታሪካዊ የመልማት እና የታላቅነት ፍላጎት በጎላ ድምፅ ተንጸባርቋል።

የሀገራችንን ሰላም ለማወክ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር የተሰለፉ ኃይሎችን በጽኑ ያወገዙት ሰልፈኞቹ፣ የኢትዮጵያ አንድነት እና እድገት በፀረ-ሰላም ኃይሎች ሴራ በጭራሽ እንደማይደናቀፍ አረጋግጠዋል። ለድል የተወለደው መከላከያ ሠራዊታችን አለኝታችን ነው።

ሀገርን ለማጽናት እና ለማበልጸግ ከመንግሥት ጎን በጽናት መቆም፣ የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ በጀግኖች ልጆቿ ክንድ ሁልጊዜም ከፍ ብሎ ይህ ሕዝባዊ ደጋፍ እና አንድነት፣ ሀገራችን ኢትዮጵያ የማትሸነፍ እና የጀመረችውን የብኀ የሚያረጋግጥ ነው።

Former Ethiopian Armed Force-የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ሠራዊት

17/10/2026

ሠራዊታችን የሕዝብ ኩራት፣ የሀገር ጋሻና የሰላም ጠባቂ ነው። ከጎናችሁ ነን! የምንችለውን ሁሉ በሕጋዊና ሰላማዊ መንገድ በማድረግ ለሀገራችን ሰላምና ደኅንነት እንተባበር።
ክብር ለመከላከያ ሠራዊታችን! ኢትዮጵያ ትኑር! 🇪🇹💚💛❤️

17/10/2026

Ethiopian for African
#ጀግኖች 🇪🇹🇪🇹

Photos from Ethiopian for African's post 17/10/2026

ስፖርት ለጤንነት፣ ለወዳጅነት፣ ለአንድነትና ለኢኮኖሚ ዕድገት!

ዛሬ 16ኛውን የአዲስ አበባ ስፖርት ምክር ቤት ጉባኤ እያካሄድን እንገኛለን። ስፖርት ጤናችንን ያሻሽላል፣ አንድነታችንን ያጠናክራል፣ የወዳጅነት ድልድይ ይሆናል፤ እንዲሁም ለከተማችን የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ዕድገት ዕድሎችን ይፈጥራል።

አዲስ አበባን የስፖርት ቱሪዝም መዳረሻ ለማድረግ የሁላችንም ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ወጣቶችን፣ ሴቶችን፣ አካል ጉዳተኞችንና ሁሉንም የማኅበረሰብ ክፍሎች በእኩልነት እናሳትፍ። ተደራሽና ጥራት ያላቸውን የስፖርት መሠረተ ልማቶች እናስፋፋ፣ እንንከባከብ፣ በኃላፊነትም እንጠቀም።

የስፖርት ዕድገት የሁላችንም የጋራ ኃላፊነት ነው። ዛሬ በስፖርት በመሳተፍ፣ ወጣቶቻችንን በመደገፍና የስፖርት መሠረተ ልማቶቻችንን በመንከባከብ የተሻለች አዲስ አበባን እንገንባ!

እናንተስ ለስፖርት ዕድገት ምን ማበርከት ትችላላችሁ?

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ!
@

Photos from Ethiopian for African's post 17/10/2026

አህጉር አቀፍ የወታደራዊ ማርችንግ ባንድ ውድድር እና ፌስቲቫል ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን ሊካሄድ ነው።

የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ጥቅምት 07 ቀን 2019 ዓ.ም
‎
‎"አንድ አፍሪካ፣ አንድ ምትና አንድ ኩራት" በሚል መሪ ቃል በአጉራችን አፍሪካ የመጀመሪያ የሆነ የወታደራዊ ማርችንግ ባንድ ውድድር እና ፌስቲቫል ሀገራችን ኢትዮጵያ ልታዘጋጅ ነው።
‎
‎በሂልተን ሆቴል የተለያዩ ሀገራት ወታደራዊ አታሼዎችና አምባሳደሮች በተገኙበት የሃሳብ ልውውጥ ተካሂዷል። በዕለቱ ሻለቃ ዲፕሎማት ተስፋዬ ወንድሙ ከመከላከያ ስፖርትና ኪነ ጥበባት ማዕከልና ከባለድርሻ አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠሩ ገልፀዋል።

በአህጉራችን የመጀመሪያ የሆነው የወታደራዊ ማርችንግ ባንድ ውድድር እና ፌስቲቫል ሀገራችን በመከላከያ የበላይ አስተባባሪነት እና በፕሪስቲጂየስ ዲፕሎማቲክ ሶልየሽንስ ኃላፊነቱ የተወሰነ ግል ማህበር አዘጋጅነት ከታሳስ 02 - ታህሳስ 05 ቀን 2019 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንደሚካሄድም ታውቋል።

ሁሉም የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት እንዲሁም በዝግጅቱ ላይ ለመሳተፍ ፍቃደኝነታቸውን ያሳዩ ወዳጅና አጋር ሀገራት የግብዣ ጥሪ የተደረገላቸው መሆኑንም ገልፀዋል።
‎
‎ከአዘጋጆች መካከል አንዱ የሆኑት ኮር ዳዊት ጌታሁን በበኩላቸው ፌስቲቫሉ የኢትዮጵያን አሁናዊ ገፅታ ለአፍሪካዊያን እንዲሁም ለአለም ለማሳየት እና የሀገራችንን ዲፕሎማሲና ቱሪዝም ለማሳደግ እድል ሊፈጥር እንደሚችል ገልፀዋል።
‎
‎የመከላከያ ሙዚቃ ኮሌጅ ምክትል ዲን ሻለቃ ዮሴፍ ይርሳው በበኩላቸው ወታደራዊ ማርችንግ ባንድ የአንድነት ምሳሌ በመሆኑ የአፍሪካ ሀገራት በአንድነት ተሰባስበው ውድድሩን ለመጀመሪያ ጊዜ በሀገራችን ማድረጋቸው መዚቃ የአለም ቋንቋ መሆኑን የሚያሳይ እና ጥሩ የሆነ የልምድ ልውውጥ ሊገኝበት የሚችል እንደሆነ ተናግረዋል።
‎
‎ዘጋቢ ሀይሌ ብርሃኑ
‎ፍቶግራፍ ገነት አወቀ

follow 👇👇👇
FDRE Defense Force - የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት

17/10/2026

"ህልማችን ትልቅ ነው፤ ትልቅ ህልም ደግሞ ትልቅ ሥራና ተጋድሎ ይፈልጋል። እያንዳንዷ ደቂቃ ለሀገር እድገትና ለትውልድ ብልጽግና መዋል አለባት።"

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ

Photos from Ethiopian for African's post 17/10/2026

"መከላከያ ሰራዊትን እናመሰግናለን"
የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች ዛሬ መከላከያን ለማመስገን ሰልፍ ወጥተዋል።

ህውሃት ሰቆጣን ለመያዝ ያለምንም እረፍት 6 ጊዜ ከባድ ማጥቃት ፈፅሞ በሠራዊቱ ጠንካራ መከላከልና ማጥቃት መክሸፉ ይታወቃል።

17/10/2026

መከላከያ ሰራዊታችን የጠላትን አከርካሪ በመሰባበር ሰሜን ኢትዮጵያን ከጠላት ተላላኪዎች ነፃ እያወጣ ነው!

የሀገር ሕልውና፣ ሉዓላዊነት፣ ነፃነትና ክብር ከማንኛውም ግለሰባዊ ፍላጎትና ጊዜያዊ ጥቅም በላይ ቅድሚያ ሊሰጣቸው የሚገቡ ታላላቅ እሴቶቻችን ናቸው። ሀገር ማለት የምንኖርባት ምድር ብቻ ሳትሆን የታሪካችን፣ የባህላችን፣ የማንነታችንና የወደፊት ተስፋችን መሠረት ናት!

ዛሬም እንደ ትናንቱ፣ ለባዕዳን ተላላኪ ከመሆንና የሀገራችንን ጥቅም ለውጭ ኃይሎች አጀንዳ ከማስገዛት ተቆጥበን፤ በራሳችን አቅም፣ በራሳችን አስተሳሰብና በሀገራዊ ጥቅም ላይ ጸንተን ሀገር ወዳድነታችንን በተግባር እያረጋገጥን እንገኛለን። ሀገርን መውደድ ማለት የራሳችንን ክብር በመጠበቅ፣ ከማንኛውም አካል ጋር በእኩልነትና በመከባበር ላይ የተመሠረተ ግንኙነት መገንባት ነው።

ጀግኖች አባቶቻችንና እናቶቻችን በጽናትና በደማቸው ያስረከቡንን ሀገርና ሰንደቅ ዓላማ በክብር ማስቀጠል የዚህ ትውልድ ታሪካዊ ኃላፊነት ነው። ታሪካችን የሚያስተምረን ትልቁ ቁም ነገር—ሀገር በቃልና በወሬ ሳይሆን በተግባር፣ በጀግንነት፣ በአንድነትና በታማኝነት እንደምትጠበቅ ነው!

የሀገር ፍቅር በሚደረግ ንግግር ሳይሆን በሚታይ ሥራ፣ በሥነ-ምግባርና ለሕዝብ ጥቅም በሚደረግ ቁርጠኝነት ይገለጻል። ዛሬም የግልና የቡድን ልዩነቶቻችንን ከሀገራዊ ጥቅም በታች በማስቀመጥ፣ ከጀግናው መከላከያ ሰራዊታችን ጎን በአንድነት መቆም የሁላችንም ወሳኝ ድርሻ ነው።

የቀድሞ ጀግኖቻችን በመስዋዕትነት ያቆዩልንን ኢትዮጵያ በበለጠ ክብርና ሰላም ለሚቀጥለው ትውልድ የማስረከብ ታላቅ አደራ አለብን!
#ኢትዮጵያ

Photos from Ethiopian for African's post 17/10/2026

🇪🇹🏇🏇
ወርቅ የሚገባቸው እናቶች ስለምን የአፈሙዝ ጩኸት ይስሙ?

የበጋውን ሙቀት ተቋቁማ፣ በክረምት ጭቃው እና ቁሩ ሳይበግራት ለስጋዎቿ ክፋይ የወደፊት ሕይወት ስትል የምትማስነው እናት ለልጆቿ ስትል የምትከፍለው ዋጋ ከሁሉም የተለየ ነው።

የማዕድ ቤቱ ጭስ ዓይኗን እያቃጠላት፤ ልጇን በጀርባዋ አዝላ ምግብን ታበስላለች። የልጇን ሕመም ታማ፤ ሳቁን ስቃ፤ ለቅሶውን አልቅሳ መከራ እና ስቃዩን ችላ ልጇን ታሳድጋለች።

"ከልጆቼ በፊት እኔን" እያለች ደስታቸውን እንጅ ሀዘናቸውን እንዳታይ ዘወትር ፈጣሪዋን ትለምናለች። እናቶች ልጆቻቸው በመልካም ስብዕና አድገው እንዲጦሯቸው፣ በመልካም ሥራቸው ስማቸውን እንዲያስጠሩላቸው፣ ለማኅበረሰቡ ኩራት፣ ለሀገሩ ደግሞ ስኬታማ ተግባርን እንዲከውኑ ይመኛሉ።

ዳሩ ግን እናቶች ልጆቻቸውን ለማሳደግ ያሳለፉት የፈተና ዘመን እና ድካም ከንቱ ሲኾን ደግሞ አንገታቸውን ይደፋሉ።

በተለይም በሀገር ጥፋት ላይ ልጆች ተሳታፊ ሲኾኑ ሀዘናቸው እጥፍ ድርብ ይኾናል። በአማራ ክልል ባለፉት ዓመታት የተፈጠረው የጸጥታ ችግር ደግሞ የእናቶችን ሀዘን አክብዶት ቆይቷል።

የሕዝብን ጥያቄ እናስመልሳለን ያሉ ታጣቂዎች በርካታ እናቶች ልጆቻቸውን እንዲያጡ፣ በአፈሙዝ ጩኸት እንዲረበሹ፣ የሕክምና አገልግሎት እንዳያገኙ፣ በሩቅ ያሉ ልጆቻቸውን እንዳያዩ፣ በነጻነት ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ አድርጓቸው ቆይቷል።

ለራሳቸው ተጎሳቁለው ልጆቻቸውን ያደመቁ እናቶች መጥፎ መንገድን በመረጡ ታጣቂዎች በእንባ ታጥበዋል።

ለልፋታቸው ወርቅ፣ ለመድመቂያቸው ነጭ ቀሚስ ሲገባቸው የአፈሙዝ ድምጽን ይሰሙ ዘንድ ተፈርዶባቸው ቆይቷል። በክልሉ ግጭት እንዲቆም፣ ሰላም እንዲሰፍን እናቶች ተደጋጋሚ የሰላም ጥሪን ሲያቀርቡ ቆይተዋል።

ስለ እናቶች ድካም ሰላምን ማጽናት፣ የሰላምን አማራጭ መቀበል፣ የአፈሙዝ ላንቃን መዝጋት ከታጣቂዎች እና ከሁሉም ማኅበረሰብ የሚጠበቅ ተቀዳሚ ተግባር ነው።

ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የመጣውን የክልሉን ሰላማዊ እንቅስቃሴ ማስቀጠል እና የእናቶችን የሰላም ተማጽኖ መቀበል ከታጣቂዎች ይጠበቃል።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በደብረ ማርቆስ የአየር ማረፊያ ምርቃት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት በአማራ ሕዝብ እየማሉ ሕዝብን የሚያደናግሩ፣ የኢትዮጵያ ጠላቶች ህልም ተጋርተው የሕዝብን ስቃይ የሚያራዝሙ አሜካላዎች መኖራቸውን አንስተዋል።

የታጠቁ አካላትን ለማስቆም ከመንግሥት ባሻገር ሕዝቡ የበኩሉን ኀላፊነት ሊወጣ እንደሚገባም አሳስበዋል። ማኅበረሰቡ የአካባቢውን ሰላም በቁርጠኝነት ማጽናት እንዳለበትም ነው የተናግሩት።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በዚሁ ጉዳይ ላይ ባደረጉት ንግግር በዓባይ ሸለቆ እና በአሊዶሮ አካባቢ የሸፈተውን ሽፍታ በጋራ ታግሎ ማስወገድ ሲገባን ተጨማሪ ሽፍቶችን ማበራከት ተገቢ አይደለም ማለታቸው ይታወሳል።

የትም ቦታ ያለ ሽፍታ በሕግ እንዲታረም በጋራ በመሥራት የሕዝብን ሰላም እና ልማት ማረጋገጥ ይገባል ነበር ያሉት። የሚለያየንን ነገር እየተወያዩ፣ ጥቃቅኑን ነገር እየረሱ፣ በትልቁ ጉዳይ መሠብሠብ፣ መተባበር እና የሁላችንም የጋራ መሻት የኾነውን ሰላም እና ልማት በጋራ ለማሥፈጸም መጣር ይበጃል ብለዋል።

ይህ ሲኾን በቀየው ሰላም ይሰፍናል፤ ሀገር ደህና ትኾናለች፤ ሕዝብም በዘላቂነት እፎይ ይላል፤ የእናቶች እንባም ታብሶ የተጨነቀ ገጻቸው በደስታ ይሞላል። ስለዚህ አሁንም ቢኾን በጫካ የሚንቀሳቀሱ ቀሪ ታጣቂዎች በሙሉ ስለእናት ሀዘን እና ስለሕዝብ ልመና ብለው የሰላም አማራጩን ፈጥነው መቀበል ይጠበቅባቸዋል።

!

!🇪

Photos from Ethiopian for African's post 16/10/2026

የትግራይ ቴሌቪዥን በቅርቡ ስርጭት ይጀምራል !!

📺

የትግራይ ቴሌቪዥን ስርጭትን ወደአየር ላይ ለመመለስ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ። የሕንጻው እድሳት እየተሰራ ሲሆን አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች እየተሟሉ ይገኛሉ።

በአሸባሪው ቡድን ተሹሞ የነበረው የትግራይ ቴሌቪዥን ዋና ሥራአስኪያጅ የትግራይ ቴሌቪዥንን የፌስቡክ ገጽ መንግስት የይለፍ ቃሉን ሰብ`ሮ ተቆጣጠረው በማለት ፈገግ እንዳሰኘን የቴሌቪዥን ስርጭት ሲጀመር ምን እንደሚለን ለመስማት በጉጉት እንጠብቃለን 😂

Category

Website

Address

Addis Ababa
GOOD

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when Ethiopian for African posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in Addis Ababa.