Lafto Woreda Five

Lafto Woreda Five

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Lafto Woreda Five, Health/Beauty, Addis Ababa.

19/07/2026
Photos from Ministry of Peace የሰላም ሚኒስቴር's post 14/07/2026
14/07/2026

የሚኒስትሩ መልዕክት

“እኛ ኢትዮጵያዊያን የስልጣኔ አብነት፣ የአብሮነት ምልክት፣ የነፃነት ፋና፣ የጥበብ ጀማሪ እና ባለብዙ ፀጋ በመሆናችን ይህን እንደ ሀገር የመመካከር ዕድል በተገቢው ተጠቅሞ ልዩነታችንን በስልጡን ምክክር መፍትሄ በመስጠት ታሪክ ሰርቶ ማለፍ አሁን ላለነው ትውልድ ትልቅ እና አይረሴ ድል ነው!

በመሆኑም በአንድም በሌላ በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩ እና ለአብሮነታችን እንዲሁም ለዘላቂ ሰላማችን እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ ለመፍታት አሁን ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሰራቱ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ስለኢትዮጵያ በሰለጠነ ንግግር እና በሰላማዊ ውይይት ለመምከር መሰባሰባቸው የሀገሬን ልጆች ብስለት፣ አርቆ አሳቢነት እንዲሁም የኢትዮጵያንም ከፍታ እና የወደፊት ብሩህ ተስፋ ያሳየን ነው።

በመሆኑም እንደ አንድ ዜጋ የተሰማኝ ደስታ ወደር የሌለው ነውና ሀገራዊ ምክክሩ የተሳካ እንዲሆን ከልብ ተመኘሁ!

We Ethiopians are symbols of civilization, benchmark of unity and horizon of freedom. We are pioneers of wisdom and wealthy of blessings. Using this national dialogue opportunity to solve our differences through civilized discussion and make history is a great, unforgettable victory for our generation!

Right now, we are focusing on identifying and solving historical issues that are obstacles for our unity and lasting peace. Ethiopians coming together nationwide to talk about Ethiopia through peaceful and civilized discussion shows the maturity and foresight of our citizens. It also shows the greatness and bright future of Ethiopia.

As a citizen, I feel endless joy and sincerely wish for the national dialogue to be ever successful!”

14/07/2026

ምላሽዎን በኮሜንት ያሳውቁን! 👇
ሰላም ለኢትዮጵያችን! ‌‌
Let us know your answer in the comments! 👇
Peace for our Ethiopia! ‌‌
#ሰላምግንባታ #ሰላማዊነት #ሰላም #ኢትዮጵያ

14/07/2026

ምክክር ለሀገራችን ዘላቂ ሰላም
እና ለኅብረብሔራዊ አንድነታችን መጎልበት ሚናው አይተኬ ነው!

ለእኛ ኢትዮጵያውያን ምክክር
✅ ለገጠሙን ችግሮቻችን መፍቻ፣
✅ ለአብሮነታችን ማጠንከሪያ፣
✅ ለግንኙነታችን ድልድል እና
✅ ከአያት ቅድመ አያቶቻችን የወረስነው አንዱ እና ትልቁ ለነገ ትልማችን ማሳኪያ እሴታችን ነው።

ስለሆነም በአንድም በሌላ በታሪክ አጋጣሚ የተፈጠሩ እና ለአብሮነታችን እንዲሁም ለዘላቂ ሰላማችን እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን ለይቶ ለማስተካከል በሀገር አቀፍ ደረጃ ኢትዮጵያዊያን ስለኢትዮጵያ ለመምከር በአንድ ከትመዋል።

በመሆኑም በሰለጠነ ንግግር እና በሰላማዊ ውይይት ሀገራዊ መግባባት ተፈጥሮ በልጆቿ የጋራ ጥረት የበለፀገች ኢትዮጵያን ለነገው ተተኪ ትውልድ ማሻገር ይቻል ዘንድ የሰላም ሚኒስቴር መልካም ምኞቱን ይገልፃል።

ሰላም ለኢትዮጵያ! 🕊️

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa