Kaffa Forest Honey

Kaffa Forest Honey

Share

From the Kaffa forests to your table � Pure, unprocessed honey – Sweeten your life today �

24/03/2026

ትክክለኛውን ማር እንዴት እንምረጥ?
✅ንጹህ እና ጥራቱን የጠበቀ ማር ለማግኘት ከአካባቢ ንብ አርቢዎች ወይም ከሚያምኑት ቦታ መግዛት ይመረጣል።
✅ጥቁር ቀለም ያላቸው የማር አይነቶች በአጠቃላይ በጠንካራ አንቲኦክሲዳንቶች የበለጸጉ ናቸው። በ እኛ አካባቢ ጥቁር ማር ለ መድሀኒትነት ያገለግላል።
✅ ማር በልክ ከተጠቀምንበት ለጤናችን እጅግ ጠቃሚ የሆነ የተፈጥሮ ስጦታ ነው።

👉እናንተስ ማርን ለምን ትጠቀማላችሁ?

22/03/2026

ማር ምን ዓይነት ንጥረ ነገሮች አሉት❓
ንጹህ የተፈጥሮ ማር [ያልተቀነባበረ] በውስጡ አሚኖ አሲድ፣ አንታይኦክሲደንት፣ ቫይታሚኖች፣ ሚኒራሎች እና ስኳር ይዟል።

🍯 What’s inside honey❓
Natural sugar • Vitamins • Minerals • Antioxidants

17/03/2026

ማር ለምን ይጠቅመናል❓

✅የበሽታ መከላከልን ማሳደግ፡ በውስጡ ባለው ንጥረ ነገር ሰውነትን ከባክቴሪያ እና ፈንገስ ይከላከላል።
✅የሳል እና ጉንፋን መፍትሄ፡ የጉሮሮ መድረቅን እና ሳልን በማስታገስ ረገድ ውጤታማ ነው።
✅ቁስል እና ቃጠሎን መፈወስ፡ በውጨኛው የሰውነት ክፍል ላይ ለሚከሰት ቁስል ፀረ-ባክቴሪያ ባህሪው ቶሎ እንዲድን ይረዳል።
✅ለቆዳ ውበት እና እርጥበት፡ ቆዳን በማለስለስ እና እርጥበትን በመጠበቅ ረገድ ጎልቶ ይታያል።
✅የምግብ መፈጨት ሥርዓትን ማገዝ፡ የአንጀት ባክቴሪያን በመመገብ መፈጨትን ያቃልላል።
✅የኃይል ምንጭ፡ በተፈጥሯዊ የካርቦሃይድሬት ይዘቱ ፈጣን ኃይል ይሰጣል።
👉ጥንቃቄዎች፡
ማር ከፍተኛ ካሎሪ ስላለው መጠኑን መጠበቅ ያስፈልጋል።

17/03/2026
Photos from Kaffa Forest Honey's post 14/03/2026

ትንሽ ስለ ንቦች 🐝
ንቦች 3 ዓይነት ናቸው፦
🔸 ንግስት ንብ (Queen Bee)
🔸 ድንጉላ ንብ (Drone Bee)
🔸 ሰራተኛ ንብ (Worker Bee)
👉ንግስት ንብ እና ሰራተኛ ንብ ሴቶች ሲሆኑ ድንጉላ ንብ ደግሞ ወንድ ነው።
👑 ንግስት ንብ
• የመንጋው አለቃ ናት
• በቀን እስከ 2000 እንቁላል ትጥላለች
• ዕድሜዋ ከ5–7 ዓመት ይሆናል
🐝 ድንጉላ ንብ
• ወንድ ንብ ነው
• ከንግስት ንብ ጋር ግንኙነት ማድረግ ብቻ ነው ስራው
🍯 ሰራተኛ ንብ
• ማር መስራት
• አበባ መቅሰም
• ንግስቷን መንከባከብ
• የሚፈለፈል እንቁላል መመገብ እና ቤት ማፅዳት
👉 በየቦታው አበባ ሲቀስሙ የምናያቸው ንቦች ሁሉ ሰራተኛ ንቦች ናቸው።

Photos from Kaffa Forest Honey's post 12/03/2026

ድንቅ የተፈጥሮ ፀጋ🌿 ንፁህ የጫካ ማር🌿🍯

በካፋ ደኖች ውስጥ፦ፏፏቴ፣ የእግዜር ድልድይ፣ ፍል ውሃ 💦፣ የተለያዩ የዕፅዋት አይነቶች፣ የአእዋፍት ዝርያዎች እና የመሳሰሉት ይገኛሉ።

🌿 In the forests of Kaffa, waterfalls nourish the land and support the rich Biosphere.

Photos from Kaffa Forest Honey's post 12/03/2026

የተፈጥሮ የጫካ ማር ለእርሶ 🍯🐝.🌿
🍯 Pure Kaffa Forest Honey Available
✔ 1kg jar
✔ 500g jar
✔ 250g jar
Natural • Unprocessed • Forest honey 🌿
📩 Contact for order.

Photos from Kaffa Forest Honey's post 11/03/2026

በካፋ ደኖች ውስጥ የሚበቅሉ የቡና ተክሎች ንቦች የ አበባ ማር(Nectar) እና የአበባ ዱቄት(Pollen) እንዲቀስሙ ይረዳቸዋል።

Coffee plants, which grow in the forests of Kaffa, serve as a significant source of pollen and nectar for bees.

Photos from Kaffa Forest Honey's post 11/03/2026

ካፋ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ የሚገኝ አረንጓዴ የምድር ገነት በመባል የሚታወቅ ዞን ነዉ።
በምስሉ ላይ የምትመለከቱት የባህላዊ ቀፎ በአከባቢው ቋንቋ (Kafinoonoo) 'Geendo' በመባል ይታወቃል።

Photos from Kaffa Forest Honey's post 11/03/2026

From the Kaffa forests to your table 🌿 Pure, unprocessed honey – Sweeten your life today 🍯

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address

Addis Ababa