Menkorer Sub-city Communication
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Menkorer Sub-city Communication, Health/Beauty, Ehiopia, Debra Markos.
27/08/2026
ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ወጪ ማዳን ተችሏል።
በመንቆረር ክፍለ ከተማ በ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ከ27 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ወጪ መዳኑ ተገለጸ።
በመንቆረር ክፍለ ከተማ በ2018 ዓ.ም የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት በተከናወኑ ልዩ ልዩ የበጎ ተግባር ስራዎች 27,153,326 ብር የመንግስትን ወጪ ማዳን መቻሉን የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ፀሐይ በለጠ ገለጹ።
የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትበክረምቱ የበጎ ፈቃድ መርሃ ግብር በርካታ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ስራዎች የተከናወኑ ሲሆን፥ ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው፦
የቤት ግንባታና ጥገና፡ ለአቅመ ደካሞችና ለችግረኛ ወገኖች የሚሆኑ ቤቶች ተገንብተዋል፤ ተጠግነዋል።
የደም ልገሳ፡ የዜጎችን ህይወት ለመታደግ የሚያስችል ከፍተኛ የደም ልገሳ ተግባር ተከናውኗል።
የተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፡ አቅም ለሌላቸው ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ተደርጓል።
አረጋውያንን ማልበስ፡ ለክፍለ ከተማው አረጋውያን የአልባሳት ድጋፍና እንክብካቤ ተሰጥቷል።
የቤተሰብ ምዝገባ፡ የማህበረሰቡን መረጃ ለማደራጀት የሚያግዝ የቤተሰብ ምዝገባ ስራ ተከውኗል።
የችግኝ ተከላና አካባቢ ጥበቃ፡ የአረንጓዴ አሻራን ለማሳረፍና የተፈጥሮ ሀብትን ለመጠበቅ ሰፊ የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ስራዎች ተከናውነዋል።
ዋና ስራ አስፈፃሚው አቶ ፀሐይ በለጠ አክለውም ለዚህ ታላቅ ስኬት መገኘት በነጻ አገልግሎት ሲረባረቡ ለነበሩት የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶችና የአካባቢው ማህበረሰብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
26/08/2026
ሠላም የሁላችንምነው
በደ/ማርቆስ የመንቆ/ክ/ከተማ አስተዳደር ከታክሲ አሽከርካሪዎች ጋር በወቅታዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አካሄደ።
ወቅታዊ የሠላም፣የአገልግሎት አሰጣጥ፣አጠቃላይ የታክሲ እንቅስቃሴና በሌሎች ዙሪ ውይይት የተደረገ ሲሆን ለውይይት መነሻ ሃሳብ ከቀረበ በኋላ ሃሳቡን መነሻ በማድረግ ተወያዮቹ ከሠላም፣ከአገልግሎት አሰጣጥ፣ከፌርማታ፣ከህገወጥነት እንዲሁም የከተማዋን ገጽታ ከመገንባት አንጻር ከመንግስትና ከታክሲ አሽከርካሪዎች ምን ይጠበቃል የሚሉትንና ሌሎችን ሃሳቦች አንስተዋል።
ለተነሱ ሃሳቦች ማብራሪያ የሠጡት የመንቆ ክ/ከተማው ፖሊስ አዛዥ ኮማንደር አልማው ወርቅዬ ሠላም የሚመጣው ከግለሰብ፣ከቤተሰብ፣ከጎረቤት እንዲሁም እንደ ሃገር በጋራ ስንሰራ በመሆኑ አሁን ያለው አንጻራዊ ሠላም እንዲቀጥል ሁላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን ብለዋል።
ኮመንደሩ አገልግሎት አሰጣጥን በተመለከተ መንግስት ሙስናን ለመከላከል ከምንጊዜውም በላይ ቆርጦ ተነስቷል ሲሉ እየሄደበት ያለውን እርቀት አብራርተው ከጸጥታ ሃይሉ ጋር በተያያዘ የተነሱ ሃሳቦችን በልኩ መገንዘብ እንደሚገባ በመጠቆም ችግሩ ካለ ግን ወስደን የምንፈታው ይሆናል ብለዋል።
ሌላው ማብራሪያ የሰጡት የክ/ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ ታክሲዎች ለማህበረሰቡ ለታመመው፣ለወደቀው፣ለቆሰለው ቀድመው በመድረስ አገልግሎት የሚሰጡና የገቢ ማግኛ የስራ ዕድል መፍጠሪያ በመሆናቸው በጥንቃቄ መስራት ይገባል።
በሌላ በኩል ታክሲዎች ለበጎም ሆነ ለመጥፎው የገጽታ ግንባታ ትልቅ አስተዋጾኦ ስላላቸው የከተማችሁን ገጽታ ለመገንባትና በበጎ ለማስጠራት መስራት ይገባል ብለዋል።
ችግሮችን በውይይት ለመፍታት መነጋገር አንዱ የመፍትሄ አካል እንደሆነ የገለጹት አቶ ፀሐይ በለጠ የፌርማታ እና ሌሎች ተሳታፊዎች መስተካከል አለባቸው ብለው ያነሷቸውን ችግሮች ወስደው ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ ተናግረዋል።
ነሐሴ 20/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
26/08/2026
ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ
በደ/ማርቆስ በመንቆረር ክ/ከተማ ሥራና ክህሎት ጽ/ቤት አመቻችነት ሥራ ፈላጊ ወጣቶች ላይ የሚሰራ "ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ" በሚባል መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ከመንግስት ጋር በመተባበር ለወጣቶች የስራ ዕድል ለመፍጠር ከባለ ሃብቶችና ተወካዮቻቸው ጋር ውይይት አካሄደ።
ድርጅቱ ከመንግስት ጋር በመተባበር ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ሥራ ለማስገባት ከባለሃብቶች ጋር በጥምረት ለመስራት የጋራ ውይይት አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት የደ/ማርቆስ ሥራና ክህሎት መምሪያ ሃላፊ አቶ መኮነን ሙሉአዳም የፕሮጀክቱ ዓላማ ሥራ ፈላጊ ወጣቶችን ወደ ሥራ ከመግባታቸው በፊት ለስራ ብቁ እንዲሆኑ ለማዘጋጀትና የሥራ ፈላጊውን ቁጥር ለመቀነስ እንደሆነ አብራርተዋል።
አቶ መኮነን የሥራ ፈላጊው ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ የስራ ፈላጊዎችን ቁጥር ለመቀነስ ፕሮጀክቱ ከመንግስት ጋር በመተባበር በኢንደስትሪ፣በአገልግሎትና በግብርና ዘርፍ ብቁ ወጣቶችን ለማሰማራት የሥራ ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ ሙሉ ሥልጠና ለመስጠት እየተንቀሳቀሠ ያለ ድርጅት መሆኑን ገልጸዋል።
ወጣቶቹ በጽ/ቤቱ በመመልመያ መስፈርት ተመልምለው በቴክኒክና ሙያ ተቋም ለ12 ቀናት ሥልጠና ከወሰዱ በኋላ በመረጡት ዘርፍ ለ6 ወራት የሥራ ልምምድ እንዲያደርጉ በማድረግና ቋሚ የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ይሰራል ብለዋል ሃለፊው።
ይህን ፕሮጀክት ተፈጻሚ ለማድረግ ባለሃብቶች ባሏቸው የስራ መስኮች የተመለመሉና በቴክኒክና ሙያ የሠለጠኑ ወጣትችን ባሏቸው ፋብሪካዎች ውስጥ ገብተው የሥራ ልምምድ እንዲያደርጉ ለማድረግ ከባለሃብቶቹ ጋር ውይይት ማድረግ እንዳስፈለገ በመግለጽ ፕሮጀክቱ እንዳይባክን በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባም አቶ መኮነን በአጽንኦት ተናግረዋል።
በክ/ከተማው የሚገኙ ባለሃብቶችም በተለይ በክልሉ ያለው የሥራ ፈላጊ ቁጥር እየጨመረ መሆኑ እንዳሳሰባቸው ገልጸው በሚቻላቸውና ተመድበው ወደ ተቋሞቻቸው የሚመጡ ምልምል ወጣቶችን ተቀብለው እንደሚያለማምዱ እና የሥራ ልምድ እንዲኖራቸው ለማድረግ እንሰራለን ሲሉ ፈቃደኝነታቸውን አሳይተዋል።
በውይይት መድረኩ የመንቆ/ክ/ከተማ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ እግዜሩ አለኸኝ፣የክ/ከተማው ሥራና ክህሎት ሃላፊ አቶ አምደወርቅ ታደሰ፣ባለሃብቶችና የባለሃብት ተወካዮች ተገኝተዋል።
ነሐሴ 20/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
26/08/2026
የ2018 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ኾኑ።
የ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ሠርቲፊኬት ፈተና ውጤት የሚገለጽባቸው አድራሻዎች ይፋ ኾነዋል። በ2018 ትምህርት ዘመን የኢትዮጵያ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች ዛሬ ነሐሴ 19/2018 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት ጀምረው የሚከተሉትን አማራጭ ማስፈንጠሪያዎች በመጠቀም ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።
ውጤት የሚገለጽባቸው ማስፈንጠሪያዎች፡-
📌በድረ ገጽ ፡ https://result.eaes.et
📌ቴሌግራም፡ https://result.eaes.et/telegram
📌አጭር የጽሑፍ መልዕክት፡ https://result.eaes.et/sms
ተፈታኞች ቅሬታ ሲኖራቸው በአካል መምጣት ሳያስፈልግ https://result.eaes.et/complaint የሚለውን ማስፈንጠሪያ በመጠቀም ቅሬታቸውን ከነሐሴ
19 እስከ 26/2018 ዓ/ም ከቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ በማቅረብ ምላሹንም በተመሳሳይ ማስፈንጠሪያ በኩል መከታተል የሚችሉ መሆኑን አገልግሎቱ ያሳውቃል።
በተጨማሪም ተፈታኞች ውጤታቸውን ከላይ ባሉት ማስፈንጠሪያዎች እንዳዩ ሠርቲፊኬታቸውን አውርደው በመያዝ ወይም በማተም ለሚያስፈልጋቸው አገልግሎት መጠቀም ይችላሉ።
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
22/08/2026
በሰላም ተከብሯል
በደ/ማርቆስ በመንቆ/ክ/ከተማ የመንበረ መንግስት እንተ ይዕቲ ደብረ ሲና ግምጃ ቤት ኪዳነ ምህረት ቤተ ክርስቲያን የእናታችን የኪዳነ ምህረት ዓመታዊ የንግስ በዓል በሰለም ተከብሯል ።
የዓመት ሰው ይበለን።
ነሐሴ 16/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
21/08/2026
⚖️⚖️⚖️⚖️⚖️
የጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የከፍተኛና የወረዳ ፍርድ ቤት ዳኞች በደብረ ማርቆስ ከተማ በመንቆረር ክፍለ ከተማ የባህል ፍርድ ቤት የስራ እንቅስቃሴን ጎበኙ።
የባህል ፍርድ ቤት በማህበረሰቡ ውስጥ ያሉ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን በሀገር በቀል እውቀት፣ በባህላዊ እሴቶችና በሽምግልና ሥርዓት ለመፍታት በሕግ ዕውቅና ተሰጥቶት የሚቋቋም አማራጭ የፍትሕ መስጫ ተቋም ነው።
በመንቆረር ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05 እና ቀበሌ 11 የባህል ፍርድ ቤት ተቋቁሞ የዳኝነት ተደራሽነትን ለማፋጠንና ወጪን ለመቀነስ በይፋ ሕጋዊ ዕውቅና ተሰጥቷቸው በሰፊው ሥራ እየሠሩ ይገኛሉ።
የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች፣ የከፍተኛና የወረዳ ፍርድቤት ሰብሳቢ ዳኞችና ባለሙያዎች በተገኙበት በመንቆረር ክፍለ ከተማ ቀበሌ 05 እየተሰራ ያለውን የባህል ፍርድ ቤት ስራ በመጎብኜት ለተመራጭ የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች/ሽማግሌዎች/ ድጋፍ አድርገዋል።
የባህል ፍርድ ቤት ዳኞች በአንድ ወር ውስጥ 16 ኬዝ በማሸማገል መፍታት መቻላቸውንም አስረድተዋል።
የባህል ፍርድ ቤት መርሆዎች
ሙሉ ፈቃደኝነት፦ ማንም ሰው ፍላጎቱና ፈቃዱ ካልሆነ በቀር በባህል ፍርድ ቤት እንዲዳኝ አይገደድም።
ዕርቅና ሰላም፦ ዋና ዓላማው አሸናፊና ተሸናፊ መለየት ሳይሆን ቂምና ጥላቻን አስወግዶ ማህበራዊ ሰላምን መመለስ ነው።
ወጪና ጊዜ ቆጣቢነት፦ ጉዳዮች በነጻና በአቅራቢያ (በቀበሌ ደረጃ) ስለሚታዩ ህብረተሰቡን ከእንግልት ያድናሉ።
ከሕገ-መንግሥቱ ጋር አለመጋጨት፦ የሚሰጡት ውሳኔዎችና የሚከተሉት ሥርዓቶች የዜጎችን ሰብአዊ መብቶችና የሀገሪቱን ሕገ-መንግሥታዊ መርሆዎች የጠበቁ መሆን አለባቸው። በሚል ግንዛቤም ፈጥረዋል።
በመጨረሻም ማህበረሰቡ የባህል ፍርድ ቤት ጥቅምን በመረዳት በአካባቢው ባህል፣ ወግና ሽምግልና ችግሮቹ እንዲፈቱ የባህል ፍርድ ቤቶችን መጠቀም እንደሚገባ ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ነሐሴ 15/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
21/08/2026
የሠው ሃብትን በአግባቡ ለመያዝና ለማወቅ የሲ/ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት እጅግ ወሳኝ ነው ሲሉ የመንቆ/ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ ተናገሩ።
.
በደብረ ማርቆስ የመንቆር ክፍለ ከተማ ሲቨልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሉት "የሰቪልና ቤተሰብ ምዝገባ ማካሄድ የማንነት ማረጋገጫ ህጋዊ ሰነድ ነው" በሚል መሪ ቃል የ2018 ዓ.ም የሲቨልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቀንን በውይይት አከበረ።
በመድረኩ ላይ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የመንቆ/ክ/ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሐይ በለጠ የሠው ሃብትን በአግባቡ ለመያዝና ለማወቅ የሲ/ቤተሰብ ምዝገባ እጅግ አስፈላጊ ነው ብለዋል።አቶ ፀሐይ የቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ማካሄድ ያለውን ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
በውይይት መድረኩ ስለ ወሳኝ ኩነት ምንነት፣ጠቀሜታ እና ተያያዥ መረጃዎች ማለትም ወሳኝ ኩነት ስለሚባሉት የልደት፣የጋብቻ፣የሞት፣የጉዲፍቻ፣የፍችና ሌሎች ኩነቶች ሰፊ ማብራሪያ በሰነድ ቀርቧል።
ሰነዱን ያቀረቡት የክ/ከተማው ሲ/ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ቡድን መሪ ወ/ሮ ጥሩዬ ብዙአየሁ የ2018ዓ.ም የምዝገባ አፈጻጸም ከ169 ፐርሰንት በላይ እንደሆነና አፈጻጸሙ በጣም ጥሩ የሚባል እንደነበር ገልጸዋል።
የመንቆ/ክ/ከተማ አስ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ጌታ ተገኘ የሲ/ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ሃገር አቀፍ ድረስ ጠቀሜታው ከፍተኛ በመሆኑ ማህ/ሰቡ ወቅቱን የጠበቀ የሲ/ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ማካሄድ እንዳለበት አሳስበዋል።
በመድረኩ የክ/ከተማው የብ/ፓ/ቅ/ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ማስረሻ ጸጋዬ፣ከመምሪያ የሲ/ቤተሰብ ምዝገባ ቡድን መሪ ወ/ሮ ሰላም ዙርባቸው፣በክ/ከተማው ካሉ ቀበሌዎች የተውጣጡ የማህበረሰሰብ ክፍሎችና ባለሙያዎች ተገኝተዋል።
ነሐሴ 15/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
20/08/2026
በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር የመንቆረር ክፍለ ከተማ “ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን በመቀልበስ ዘላቂ ሰላምና ልማትን እናረጋግጣለን” በሚል መሪ ቃል ከጠቅላላ የመንግስት ሰራተኞች ጋር የምክክር መድረክ ተካሄደ።
የምክክር መድረኩ ዋና ዓላማም በሀገር፣ በክልላችን፣በከተማችንና በክፍለ ከተማ ደረጃ የሚስተዋሉ የሰላምና የፀጥታ ስጋቶችን በጋራ በመገምገም፣ ውጫዊ የወረራ ስጋትንና ውስጣዊ የፅንፈኝነት አደጋን ለመቀልበስ የሚያስችሉ የጋራ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ እንዲሁም ሰላምን ከልማት ጋር በማስተሳሰር የመንግስት ሰራተኛውን ሚና ማጠናከር እንደሆነ ተጠቅሷል።
ነሐሴ 14/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
19/08/2026
በደብረ ማርቆስ የመንቆረር ክፍለ ከተማ ሴቶች ክንፍ ከየቀበሌው ለተውጣጡ ሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
ድጋፉ የተደረገው ለተጋላጭና ወጣት ሴቶች ሲሆን ድጋፉ በክ/ከተማው ሴቶች ክንፍ አሰባሳቢነት ከደ/ማርቆስ ስፔሻላይዝድ ሪፈራል ሆስፒታል የተገኘ ነው ተብሏል።
ነሐሴ 13/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
17/08/2026
የደብረ ማርቆስ ከተማ መንቆረር ክፍለ ከተማ ቀበሌ ዐ5 አስተዳደር ከልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር ዙሪያ የህዝብ ውይይት አካሄደ።
የውይይቱ ዋና ዓላማ በክፍለ ከተማውና በቀበሌው የሚታዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በጋራ መለየት። በሰላም፣ በልማት እና በመልካም አስተዳደር እቅዶች ዙሪያ ከህብረተሰቡ ጋር መግባባት ላይ መድረስ። የህዝቡን የልማትና የመልካም አስተዳደር ጥያቄዎች በውይይትና በምክክር መፍታትና ሰላማዊ ከባቢ መፍጠር ለዚህም ህዝብን ባለቤት ማድረግ ነው ተብሏል።
በቀጣይም ህብረተሰቡን ያሳተፉ መሰል የውይይት መድረኮች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተመላክቷል።
ነሐሴ 11/2018ዓ.ም
መንቆረር ክ/ከተማ ኮሙኒኬሽን
የፌስ ቡክ ገጻችንን ለመወዳጀት ሊንኩን ይጫኑ
https://www.facebook.com/profile.php?id=61577372172164&mibextid=ZbWKwL
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Debra Markos
