Jinka General Hospital
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Jinka General Hospital, Health/Beauty, Jinka Town, Jinka.
25/04/2024
እንኳን ደስ አላችሁ!!
የጅንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተከታታይ ሙያ ማሻሻያ ስልጠና (CPD) ማዕከልነት ተመርጣ ዕውቅና ተሰጠው። ላለፉት ጊዜያት ለብቃት ማረጋገጫ እንድሰው አመልክታ አስፈላጊውን ዝግጅት ሲያደርግ የቆየው ሆስፒታላችን የብቃት ማረጋገጫውን ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና አጠባበቅ መኮንኖች ማህበር አገኝቷል፡፡ ሁሉም የጤና ባለሙያ የሥልጠና ክፍተቱ እየተለየ በዕቅድ አቅም ለመገንባት ብሉ፥ የሙያ ፈቃድ ለማደስ ዝቅተኛ ተፈላጊ የሥልጠና ሰርተፊኬት ወይም ክሬዲት ሃወር ቢሉ፥ ከእንግዲህ እኛን ያማክሩ!! በሆስፒታላችን ዙሪያ ባሉ ዞኖችና ወረዳዎች ያላችሁ በጤናና ጤና ነክ ዘርፍ የተሰማራችሁ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሀገር በቀል መንግስታዊና መ/ያ/ድርጅቶች፣ የግል ተቋማት ወዘተ... ሀሳቦንና የሥልጠና ዕቅድዎን ይዘው ጠጋ ብለው ያማክሩን። ከዚህ ውጪ ጤናማ ሥልጠና ሁሉ ሰርቲፋይ ስለሚሆን ከCPD ሥልጠና ማዕከል ውጭ አሊያም ከማዕከላችን ዕውቅና ውጪ የሚሰጥ የጤና ሥልጠና እንደማይፈቀድ ብቻም ሳይሆን ተገቢነት የሌለው መሆኑን እየገለጽን በድጋሚ ጉዳዩን በጉጉት ስትጠብቁ ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ብለናል።
.
20/03/2024
መልካም ዜና ለጂንካ ከተማ
11/03/2024
በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል በቀን 30/6/2016 የመጀመሪያው የኤችአይቪ ካችመንት ኤሪያ ስብሰባ ተካሂዷል:: በዚህም መረሃግብር የሶስት ወር አፈፃፀም ተገምግሞ በሆስፒታሉ ሜዲካል ዳይሬክተር ዶ/ር ብሩክታዊት አሰፋ እንዲሁም ከዞን CDC ተወካይ አቶ ፍርዱ የመፍትሄ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል:: በተጨማሪም Cryptococcal Meningitis ልየታ ምርመራ እንዲሁም ህክምና ማስጀመሪያ መረሀግብር የተካሄደ ሲሆን ገለፃውን ዶ/ር ብስራት ግርማ ሰተዋል::
03/03/2024
በጂነካ አጠቃላ ሆስፒታለ በቀን 21/6/016 ዓ.ም የሆስፒታሉ ቦርደ አመራር ግምገማ አካሄዷል፡፡ ቦርዱ በመጀምሪያ በሆሰፒታሉ ዙሪያ የተጀመሩትን የግንባታ ስራ የተመለከተ ሲሆን በዲፕሎማሲ በ MSF በኩል እየተገነባ ያለዉን የ visceral leishmaniasis ተኛቶ ህክምና ክፍል ተመልክቷል፡፡ እንዲዚህ አይነት የዲፕሎማሲ ስራዎች እንደሚበረታቱም ተቀምጧል፡፡ በመቀጠለም ብዙ ጊዜ ቅሬታ የሚነሳበት እና ከተገነባና እደሳት ከተደረገለት የቆየዉን የድንገተኛ ክፍለ አይተዋል ፤በዚህም ጉብኝት በትንሽ ወጪ እየታደሰ ያለዉን ይንድገተኛ ክፍል ከተመለከቱ በሁዋላ ሆስፒታሉ አሁን እያካሄደ ያለውን creativity አድንቀው እድሳቱም ላይ ሊያስፈለግ የሚችሉ ግበዓት እንደሚያግዙ ቃል ገበተው የጉብኝት ስረዓቱ አልቋል፡፡ በመቀጠል የሆስፒታሉን የስድስት ወር አፈፃፀም የተገመገመ ሲሆን በቀጣይም እንዴት መክሄድ እንዳለበት አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በተጨማሪ አሁን ካለዉ የኑሮ ንረት ጋር ተያይዞ አንዳንድ ጥቃቅን የሆኑ የእናቶች አገልግሎት አሰጣጥ ሁኔታ እንዲሁም ሌሎች አገልግሎቶች ላይ የዋጋ ማሻሻያ እንዲደረግ ማናጅመንቱ ያስቀመጠው መንገድ ላይ ውይይት ተደርጎ፤ ካለዉ የመዳኒት እንዲሁም የተለያዩ የገበዓት ገበያ ንረት አንፃር አንዳነድ ጥቃቅን ማሻሻያዎች እንዲደረጉ ተወስኗል፡፡ በስተመጨረሻም ሆሰፒታሉ ወደ ሌላ ተቋም ለተሻለ ህክምና ብሎ ከሚልካቸዉ ታካሚዎች ዉስጥ በቁጥራቸዉ በርከት ያሉት ለተለያዩ የ imaging modality መሆኑ ከተገለፀ በሁዋላ ከነዚህም ውስጥ በቁጥር በዛ ያሉት ለ CT scan፤MRI፤ hemodialysis እንደሆነ ተቀምጧል፡፡ ይህንንም ችግር ለመፍታት የሆሰፒታሉ ማናጅመንት ያቀረበውን የ ሜዲካል ማሽን ፈንድ ፕሮጀክት ሃሳብ የሆስፒታሉ ቦርድ አመራር በሙሉ ድምፅ ይዉንታ አጊኝቷል፡፡ ይህም ፐሮጀክት የወረቀት ስራዎችን ከጨረሰ በሁዋላ በይፋ ሆሰፒታሉ የማስጀመሪያ መረሃግበር አድርጎ የሚያሳውቅ ይሆናል፡፡
ሰላም
ይህ ይፋዊ የሆነው በጂንካ አጠቃላይ ሆስፒታል የተመሠረተ አዲሱ የ face book ገፅ ነው::
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Jinka
