Nin Dhufaa Na Eegi

Nin Dhufaa Na Eegi

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Nin Dhufaa Na Eegi, Health/Beauty, Ganda Waddeessa, Kombolcha.

03/04/2026
03/04/2026

በኢትዮጵያ የነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ የሚታየው ችግር ውስብስብና ዘርፈ ብዙ ቢሆንም፣ በአሁኑ ወቅት በአንዳንድ ተቃዋሚ ነን ባይ ግለሰቦች የሚሰነዘረው ሂስ ግን ካለበት ተጨባጭ እውነት ይልቅ ለፖለቲካ ትርፍ ተብሎ የሚደረግ የለየለት ስም ማጥፋትና የጅልነት ድራማ ሆኗል። እርግጥ ነው፣ በመንግስት መዋቅር ውስጥ ባለው የአሰራር ድክመት፣ የቁጥጥር መላላትና በአንዳንድ አመራሮች ዘንድ በሚታየው ከፍተኛ የሙስና አባዜ ምክንያት የነዳጅ ኮንትሮባንድና ህገ ወጥ ንግድ ተንሰራፍቶ ህዝቡን ለእንግልት እየዳረገው መሆኑ የማይካድ ሀቅ ነው፤ ይሁን እንጂ እነዚህ "ተቃዋሚ ነን" ባዮች ችግሩን በምክንያታዊነትና በማስረጃ ደግፈው ከመተቸት ይልቅ፣ መንግስት የዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ጭማሪንና የሀገር ውስጥ የድጎማ ፖሊሲ ማሻሻያን ተከትሎ የሚወስዳቸውን አስፈላጊ የሪፎርም እርምጃዎች ሳይረዱ በደፈናው "መንግስት ሆን ብሎ ህዝቡን ሊያስርብ ነው" እያሉ የሚነዙት ፕሮፓጋንዳ እጅግ አሳፋሪ ነው።

መንግስት የነዳጅ ድጎማን በሂደት ለማንሳትና የዲጂታል ክፍያ ስርዓትን (Telebirr/CBE) በመዘርጋት ኮንትሮባንድን ለመቀነስ የሚወስዳቸው እርምጃዎች የረጅም ጊዜ ሀገራዊ ፋይዳቸው የጎላ ቢሆንም፣ እነዚህ አካላት ግን ምንም አይነት የተሻለ አማራጭ ሀሳብ ሳያቀርቡ፣ ለሚታየው እጥረት ሁሉ መንግስትን ብቻ ተጠያቂ በማድረግና ያለ በቂ መረጃ ህዝብን በማሸበር ላይ ተጠምደዋል። ይህ ያለ ምንም ማስረጃ የሚደርግ ጩሀት፣ ችግሩን የማይፈታ ነገር ግን በጥላቻ ፖለቲካ ላይ ብቻ የተመሰረተ ትችት፣ መንግስት ውስጥ ያለውን ትክክለኛ ሙስና በቁጭት ለመታገል የሚያስችል ሳይሆን፣ ይልቁንም የህዝቡን ብሶት ለግል ዝናና ለፖለቲካ ፍጆታ ለመጠቀም የሚደረግ ባዶ ጩኸት በመሆኑ ሊወገዝ ይገባዋል።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Kombolcha?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Culinary Team

Attire

Website

Address

Ganda Waddeessa
Kombolcha