Ay Male Saro?
አዳድስ ማስታውቅያ
21/06/2026
1ኛ ቆሮንቶስ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ የመስቀሉ ቃል ለሚጠፉት ሞኝነት፥ ለእኛ ለምንድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነውና።
…
²¹ በእግዚአብሔር ጥበብ ምክንያት ዓለም እግዚአብሔርን በጥበብዋ ስላላወቀች፥ በስብከት ሞኝነት የሚያምኑትን ሊያድን የእግዚአብሔር በጎ ፈቃድ ሆኖአልና።
…
²³ እኛ ግን የተሰቀለውን ክርስቶስን እንሰብካለን፤ ይህም ለአይሁድ ማሰናከያ ለአሕዛብም ሞኝነት ነው፥
²⁴ ለተጠሩት ግን፥ አይሁድ ቢሆኑ የግሪክ ሰዎችም ቢሆኑ፥ የእግዚአብሔር ኃይልና የእግዚአብሔር ጥበብ የሆነው ክርስቶስ ነው።
19/06/2026
ቃልህ ቃልህ...
19/06/2026
!
ማርቆስ 16
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁵ እንዲህም አላቸው፦ ወደ ዓለም ሁሉ ሂዱ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።
¹⁶ ያመነ የተጠመቀም ይድናል፥ ያላመነ ግን ይፈረድበታል።
¹⁷ ያመኑትንም እነዚህ ምልክቶች ይከተሉአቸዋል፤ በስሜ አጋንንትን ያወጣሉ፤ በአዲስ ቋንቋ ይናገራሉ፤ እባቦችን ይይዛሉ፥
¹⁸ የሚገድልም ነገር ቢጠጡ አይጎዳቸውም፤ እጃቸውን በድውዮች ላይ ይጭናሉ እነርሱም ይድናሉ።
¹⁹ ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።
²⁰ እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፥ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፥ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።
19/06/2026
.
19/06/2026
በUSA በሜሪካን ሀጌር የMinsota አስቴዳዴር...
18/06/2026
በጋሞ ዞን መዋቅር ውሰጥ ሆኖ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተፈጸመ በሚገኝበት ምርጫ ክልል የገዥው ፓርቲ ክስ ውድቅ መደረግን ተከትሎ የተደራጀ የዘር ማጥፋት እንቅስቃሴ በመቀስቀሱ ዳግም በህዝብ የተመረጠው ተወካይ አስቸኳይ የፌደራል መንግስት ጠልቃ እንዲገባ ጠየቀ
በ7ኛው ብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል ገዥው የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ሽንፈት መከናነቡንና ያቀረበው የፈጠራ ክስ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሙሉ በሙሉ ውድቅ መደረጉ ታውቋል።
ይህንን ይፋዊ ውሳኔ ተከትሎ ውጤቱን ባልተቀበሉ የአካባቢው የመንግሥትና የጸጥታ መዋቅሮች አማካኝነት ዛሬ ሰኔ 11 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በአካባቢው አርሶ አደሮች ላይ መጠነ-ሰፊ የጦርነት ትንኮሳ፣ የቤት ማቃጠልና የከብቶች ዝርፊያ መጀመሩን WT Media ከአካባቢው ነዋሪዎችና ከባለሥልጣናት ያሰባሰበው መረጃ ያረጋግጣል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም በቁጥር አ1162/11/841 በወጣው ይፋዊ ደብዳቤ መሠረት የጋሞ ዞን እና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ “በዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል የምርጫ ሕግ ጥሰት ተፈጽሟል” በማለት ያቀረበውን አቤቱታ ሙሉ በሙሉ ውድቅ አድርጎታል።
ቦርዱ ጉዳዩን ለማጣራት ራሱን የቻለ አጣሪ ጉባኤ (ኮሚቴ) በማደራጀት በአካባቢው ላይ ሰፊ ማጣራትና ዝርዝር ምርመራ ሲያካሂድ ቆይቷል።
የተደራጀው አጣሪ ጉባኤ ባደረገው ጥብቅ ምርመራ ብልፅግና ፓርቲ በምርጫ አስፈጻሚዎችና በዕጩዎች ላይ ያቀረበው ቅሬታና ክስ ምንም ዓይነት በቂ ማስረጃ ያልተደገፈና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር የማይገናኝ መሆኑን አረጋግጧል።
በዚህም መሠረት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፓርቲውን ክስ ውድቅ ማድረጉን በይፋ ያሳወቀ ሲሆን በዚህም በአካባቢው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ፓርቲ ተፎካካሪዎች የክልል እና የፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ውክልና አግኝተው መመረጣቸው በይፋ ተረጋግጧል።
የጋሞ ዞን እና የአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ብልፅግና ፓርቲ ካለፈው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማግስት ጀምሮ በዘይሴ አካባቢ በሚንቀሳቀሱ ተፎካካሪ ፓርቲዎች፣ ዕጩዎችና የምርጫ አስፈጻሚዎች ላይ "በሬ ወለድ" የፈጠራ ክሶችን በማቅረብ የሕዝብን ድምፅና ፍላጎት ለማፈን ሲሞክር የቆየ ቢሆንም ሕዝቡ ግን መዋቅራዊ ጫናዎችን በመቋቋም የኢዜማ ዕጩዎችን መምረጡ ታውቋል።
WT Media ከአካባቢው ነዋሪዎች ያገኘው መረጃ መሠረት በዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልል ከተካሄደው 7ኛው ጠቅላይ ምርጫ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተሰጠውን ውሳኔ ተከትሎ በአካባቢው ከፍተኛ ግጭትና ጦርነት መቀስቀሱን ነዋሪዎች ገልጸዋል።
የምርጫ ቦርድን ውሳኔ ያልተቀበሉ የወረዳውና የዞኑ አመራሮች ግጭት በመጠንሰስ የጋሞ ተወላጆችን በዘይሴ መልክዓ-ምድር ላይ በማሰማራት የአርሶ አደሮችን ከብቶች እና የፍየል መንጋዎች ከጋጣ ማዘረፍ ጀምረዋል።
ጦርነቱ ዛሬ በቀን 11/2018 ዓ.ም. ጠዋት 4:00 ሰዓት ገደማ በጋርዛታ በኩል የክልሉ ልዩ ኃይል እና የጋሞ ተወላጆች በአንድነት በዘይሴ አካባቢ በልዩ ስሙ “ሻንካ” ወደሚባለው አካባቢ በኃይል በመግባት ተጀምሯል።
እነዚህ መዋቅራዊ ታጣቂዎች የአካባቢው አርሶ አደሮች የለፉበትን የበቆሎና የጠፍ ምርት በቀጥታ እየዘረፉና በእሳት እያቃጠሉ የሚገኙ ሲሆን የአርሶ አደሩን ከብቶችና ፍየል ጭምር እየዘረፉ ነው።
ይህንኑ ተከትሎም በአሁኑ ሰዓት በአካባቢው አርሶ አደሮች እና በተሰማሩት አካላት መካከል የክልሉን የጸጥታ አካላት ባካተተ መልኩ ከፍተኛ የተኩስ ልውውጥ እና ጦርነት እየተካሄደ ሲሆን ውጊያው በከፍተኛ ሁኔታ ተባብሶ ቀጥሏል።
በዘንድሮው ምርጫ የዘይሴ ልዩ ምርጫ ክልልን ወክለው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት (ፓርላማ) ዕጩ ሆነው ቀርበው ለሁለተኛ ጊዜ በከፍተኛና እጅግ ሰፊ በሆነ ድምፅ የተመረጡት የአካባቢው ተወላጅ አቶ አብራሃም አሞሼ ከአካባቢው ሆነው ለWT Media በሰጡት ቀጥታ ቃለ-መጠየቅ መሬት ላይ ያለውን አሳዛኝ እውነታና የትግል ሂደት በዝርዝር አስረድተዋል።
አቶ አብርሃም እንደገለጹት አስቀድሞ በምርጫው ዕለት በብልፅግና ፓርቲ አመራሮች በኩል በሕዝብ ላይ የሚፈጸሙ አደጋዎችና ዛቻዎች እንደሚኖሩና አመራሮቹም ሲፎክሩ ስለነበር ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በተደጋጋሚ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ በአካባቢው ገብቶ እንዲያረጋጋና የሰላም ዕድል እንዲፈጥር ፓርቲያቸው ጠይቆ ነበር።
በዚሁ ስጋትና ጥያቄ ምክንያት ምርጫ ቦርዱ ራሱ ኮሚቴ አዘጋጅቶ ወደ ዘይሴ ምርጫ ክልል ልኳል። የምርመራ ቡድኑ እዚያ ሄደው ከምርጫ አስፈጻሚዎች፣ ከሀገር ሽማግሌዎች፣ ከሃይማኖት አባቶችና ከሲቪል ማኅበራት አካላት ጋር ተገናኝተው አናግረዋል።
ማኅበረሰቡም "እስካሁን የተገደልን ኖረናል፣ ብዙ ችግር ተፈጥሮብናል፣ አብዛኛው ሰው ታስሯል፣ ገሚሱ ከአካባቢው ተሰዷል፣ የሞተው ሞቷል፤ የቀረው ሕዝብ መንግሥት ባመጣው ዕድል ምርጫውን በሰላም መምረጥ እንዲችል ገዳይ የሆነው ኃይል ማለትም የደቡብ ክልል ልዩ ኃይል፣ የጋሞ ዞን መደበኛ ፖሊስና ሚሊሻዎች ይውጡልን፤ የሀገር መከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ እንዲገባ ይደረግ" የሚል ሐሳብ አንስተዋል።
ይህንን የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤትና በቦርዱ የተሰየሙት አካላት አረጋግጠው ለቦርዱ በማቅረባቸው፣ በምርጫው ዕለት በቀን 24 የሀገር መከላከያ ሠራዊትና የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮ ምርጫው ተከናውኗል።
ነገር ግን በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ በተለይ በዘይሴ ዳምብሌ አካባቢ ባሉት ሦስት የምርጫ ጣቢያዎች በዘይሴ ኤልጎ ሁለት የምርጫ ጣቢያዎች እና ፋንጎ በሚባል የምርጫ ጣቢያ ላይ የብልፅግና ፓርቲ የቀበሌ አመራሮች፣ የወረዳ አመራሮችና ታጣቂ ሚሊሻዎች ለመረበሽ ከባድ ሙከራ አድርገዋል።
ፋንጎ ላይ ከ14 እስከ 16 አካባቢ ሰዎችን በጥፊና በዱላ ከባድ ድብደባ ፈጽመው ከሰልፍ አባረዋቸዋል። የፌደራል ፖሊስ ገብቶ ሲቆጣጠራቸው ሾልከው ይጠፋሉ፤ ፖሊሱ ወደ ታች ወደ ሉዳ አካባቢ ሲሄድ ደግሞ ተመልሰው ሕዝቡ በሰላም እንዳይመርጥ ያውኩ ነበር።
ከቀኑ 10:15 ጀምሮ በዘይሴ ዳምብሌ ላይ ሙሉ በሙሉ ልዩ ኃይሎችና ፖሊሶች፣ ሚሊሻዎች ምርጫውን ያቆሙ ሲሆን፣ የብልፅግና ፓርቲ የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪ ምርጫው እንዲቆም ትእዛዝ አስተላልፏል።
እስከ 12:00 ሰዓት ካቆሙ በኋላ ቦርዱ እስከ ምሽቱ 3:00 ሰዓት ይቀጥል ቢልም ከምሽቱ 1:00 ጀምሮ እስከ 6:00 ሰዓት እየከደኑ በአንዱ ጣቢያ 580 ሰው፣ በሌላው 400 ምናምን ሰው በድምሩ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ሳይመርጥ ወደ ቤቱ እንዲመለስ ተደርጓል።
ነገር ግን ሕዝቡ መዋቅራዊ ጫናዎችን ተቋቁሞ የጨከኑት መርጠው በከባድና ሰፊ ድምፅ ኢዜማን አሸናፊ አድርገዋል።
አቶ አብርሃም ስለ ሕዝቡ ምርጫ ሲያስረዱ በተፈጥሮው የዘይሴ ሕዝብ ከአፄ ምኒልክ ዘመነ መንግሥት ጀምሮ የመንግሥትን ጥቅም የሚያውቅ ሕግና ሕገ-መንግሥትን እጅግ የሚያከብርና የሚታዘዝ ሕዝብ ነው ብለዋል።
ነገር ግን በአሁኑ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መዋቅር፣ ከወረዳ፣ ከዞን እስከ ክልል ባሉት ደረጃዎች ላይ ከፍተኛ የሆነ የአንድ ብሔረሰብ የበላይነትና በአንድ ብሔረሰብ የሚመራ ሁኔታ አለ።
ያ የገዥው አካል ብሔረሰብ ተወላጅ የሆነ መዋቅር በአንድነት በመተባበር የዘይሴን ብሔረሰብ ከራሱ ካለው ከዘይሴ መልክዓ-ምድር አጥፍቶ መሬቱን ለመውረስና ለራሱ ብሔረሰብ እዚያ ለማስፈር የታቀደ የተደራጀ የዘር ማጥፋት ዕቅድ ስላለው በየጊዜው ይገድሉታል።
ሕዝቡ ማን ምን ዓይነት በደል እያደረሰበት እንደሆነ ስለሚያውቅ እና ኢዜማ የሕዝብ ዓይን፣ ጆሮና አንደበት ሆኖ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ጭምር ከአንድም ሁለት ጊዜ የዘይሴ ሕዝብ መበደልና ሕገ-መንግሥታዊ የራስ አስተዳደር ጥያቄ ያለመመለስ ሁኔታን በጥልቀት ስላነሳ ሕዝቡ መርጧቸዋል።
ይህ ድምፅ የፌደራል መንግሥቱን በመጥላት ሳይሆን “መንግሥት ይስማኝ፤ እየመረጥኩት ያለሁት አንደበት ሊሆነኝ የሚችልንና ለመንግሥት ድምፄን አሰምቶ የመዋቅር ጥያቄዬን ምላሽ እንዲያስገኝልኝ ነው” በሚል እምነት የሰጠው ድምፅ ነው ብለዋል።
ዛሬ ከነጋ ጀምሮ በዘይሴ ዳምብሌ፣ ኦጎሌና ጋርዘታ በሚባሉ አካባቢዎች (በተለይ ዳምብሌ ሰው በሚባለው ቦታ) ከገረሴ ዙሪያ ወረዳ የመጡ የደሬሼ ዙሪያ ፖሊሶች እና ታጣቂ ሚሊሻዎች አንድ ላይ በመተባበር ወደ ዘይሴ በመግባት የአርሶ አደሮችን ከብቶች፣ ፍየልና በግ ሳይቀር እየነዱ፣ እያረዱና በቀጥተኛ ዘረፋ እየወሰዱ መሆኑንና በሰላማዊ ሕዝብ ላይ ተኩስ እንደከፈቱ አቶ አብርሃም አረጋግጠዋል።
አካባቢው ከፍተኛ የሆነ የትርምስና የውጊያ ቀጠና እንዲሆን በክልሉና በዞኑ አመራሮች ሆን ተብሎ እየተፈጸመ ያለ መዋቅራዊ ጥቃት መሆኑን ጠቅሰዋል።
አቶ አብርሃም በመጨረሻም ለደቡብ ኢትዮጵያ ክልል 12 ዞን ሕዝቦች፦ የክልሉ መዋቅር ፍትሐዊና ሰላማዊ ትግል እየታገለ ያለን ሕዝብ ከገዛ ቀየው እያስገደለ በመሆኑ በልዩ ኃይል ወይም በአድማ ብተና መዋቅር ውስጥ ሆነው መጥተው የዘይሴን ሕዝብ እየገደሉ ያሉ ልጆቻቸውን መክረው ከዘይሴ ሕዝብ ላይ እጃቸውን በአስቸኳይ እንዲያነሱ፤
እንዲሁም የፌደራል መንግሥት በሰላም የተጠናቀቀውንና የሕዝብ ድምፅ በይፋ የታወቀበትን የምርጫ ውጤት በማክበር፣ የዘይሴን ሕዝብ የልዩ ወረዳ የመዋቅር ጥያቄ በአስቸኳይ በመመለስ በአካባቢው ላይ ዘላቂ ሰላም እንዲያወርድ በጥብቅ ጠይቀዋል።
WT Media በዘይሴ አካባቢ እየተካሄደ ያለውን ጦርነትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በቅርበት እየተከታተለ ተጨማሪ መረጃዎችን ለሕዝብ ይፋ የሚያደርግ ይሆናል።
18/06/2026
አስቸኳይ መልዕክት📢
በዎላይታ ዞን ከ2010 - 2014 ዓ.ም የተመረቃችሁ ሥራ አጦች በሙሉ ዛሬ ሐሙስ ጠዋት ሁላችንም ተሰብስበን ወደ ወላይታ ዞን አስተዳደር ቢሮ ስለምንገባ እንዲትዘጋጁ እናሳስባለን።
-via inbox
18/06/2026
''የኢኳቶሪያል ጊኒ መንግስት ሙሉ ካቢኔውን በመያዝ ስልጣን ለቀቀ'' በአፍሪካ ለመጀመሪያ ጊዜ ስልጣን በቃኝ ያለ መንግስት አድርጎታል!
አህጉሪቱ በነፃነት ስም ከባዕዶቹ ቀኝ ገዢዎች ነፃ ወጥታለች ብትባልም ስልጣን ያቋመጣቸዉ መሪዎቿ እኔ እሻላለሁ በሚል ዙፋኑን ከተቆናጠጡ በኋላ ህዝባቸውንና የሀገራቸዉን ዜጋ እንደ መድሀኒት መሞከርያ እንስሳት የክፉ ነገሮች መፈተሻ በማድረግ
የግፍ ግፍ መፈፀም መገለጫቸው ነዉ ።
ከአንድ ምንጭ የተቀዱ ይመስል የኋላቀርነቱ ምንጭ የሆነው ለዘመናት በአፍሪካ ህዝቦች ላይ ተጭኖ የቆየው አምባገነናዊ አገዛዝ ምክንያት ባለጊዜዎች ወንበሩን እስኪቆጣጠሩ ለዜጎቻቸውም የተስፋ ዳቦን ከመመገብ በተጨማሪ የዕለት ጉርስ የሚቀመስ በሚናፍቅ ዜጎቻቸው ስም ሳይቀር እየለመኑ ልማት በሚዲያ የሚሰራጭ ተስፋ እየመገቡ የድሎት ኑሮአቸውን መኖር መገለጫቸው ስለመሆኑ ነጋሪ አያሻውም፡፡
አሀገሩ ባለው የተፈጥሮ ሃብት አይታማም። ውድ ከሆኑ ማዕድናት፣ ነዳጅና የተፈጥሮ ጋዝ፣ በርካታ ወንዞች፣ የቁም እንሰሳት፣ ስራ ፈት የሆኑ ለንግድ ምቹ የሆኑ የባህር በሮች እና በተፈጥሮ ቱሪዝም የበለፀገ ቢሆንም የአምባገነን መሪዎች ግዴለሽነት ከአቅራቢያው አረብ ሀገራት እስከ ምዕራባውያን ፍላጎቶች የሚርመሰመሱበት
የሚዘርፉት ሁኗል ።
በተለይ በፖለቲካው መድረክ በጦር መሳሪያ ወደ ስልጣን ከመጡት ውጭ የብዙሃን ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፎ የማይስተናገድበት ሲሆን፤ ሐሳብን በነፃነት መግለፅና የፕሬስ ነፃነት ተግባራት በሽብር የሚያስቀጡ ከባድ ወንጀሎች ነው።
በተለይ ፍትህ ፣ዴሞክራሲ፣ እኩልነት፣ የፕሬስ ነፃነት ሐሳብን በነፃነት የመግለፅ እና የሰብዓዊ መብት በግልፅ የሚጨፈለቁበት የአምባገነን ጣዖታት መሪዎች ልዩ ግዛት ነው ማለት ይቻላል።
በአንፃሩ ገዥዎች በይፋ የሚፈፅሙት የሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብት ረገጣ፥ ሙስና እና በስልጣን መባለግ እንደልማትም የሚቆጠርበት ምድር ሁኗል ።
በሀይል ወይም በማታለል ስልጣን የያዙትም ለዜጎች አንዳችም ነገር ባይሰሩም የያዙትን ወንበር መልቀቅ አልቻልኩም ማለት የሞት ሞት አድርገው ነዉ የሚያዩት። እነሆ ከሰሞኑን ግን በዚህች አሳዛኝ ምድር ይሆናል ተብሎ የማይታሰብ ተደርጎም የማያዉቅ ታላቅ ሀገር ወዳድነት የታየበት ተግባር ተፈፀመ ።
የኢኳቶሪያል ጊኒ ካቢኔ በሙሉ የመንግስትን ግቦች ማሳካት ባለመቻሉ ከስልጣን መልቀቃቸውን ምክትል ፕሬዝዳንት ቴዎዶሮ ንጌማ ኦቢያንግ ማንጌ ተናግረዋል።
እንደ ኦቢያንግ ገለጻ አስተዳደሩ ከታቀዱት ግቦች 10% ብቻ በመስራቱ ይህም ከሚጠበቀው በታች ስለሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ማኑዌል ኦሳ ንሱ ንሱጋ የመንግስትን የስራ መልቀቂያ ማስገባታቸውን አስታውቀዋል።
ምንም እንኳን ኢኳቶሪያል ጊኒ በአፍሪካ ግንባር ቀደም የነዳጅ አምራች ብትሆንም፣ በኢነርጂ ዘርፍ ላይ ያላትን ጥገኝነት የዜጎችን ህይወት መቀየር አለመቻል የልማት ፕሮጀክቶች መዘግየቶችን እና የአገሪቱን ኢኮኖሚ በማባዛት ረገድ እድገት አለመኖርን ጨምሮ በርካታ ጉድለቶችን በመኖራቸው ከእኔ የተሻለ ቢመራት ይሻላል ሲሉ በሰላማዊ መንገድ ስልጣናቸውን አስረክበዋል ።
የኢኳቶሪያል ጊኒ ገዢ ፓርቲ ወይም PDGE ፕሬዝዳንቱ በመንግስት አፈጻጸም እርካታ እንደሌላቸው ተናግረዋል ይህም ሙስና የልማት ፕሮጀክቶች መዘግየቶች እና ኢኮኖሚውን ለማባዛት አለመቻላቸውን ጠቅሰዋል።
ፕሬዝዳንት ኦቢያንግ ከ1979 ጀምሮ የመካከለኛው አፍሪካን ሀገር ሲመሩ ከመቆየታቸው አንፃር አዛዥ ናዛዥ የሆኑበትን ስልጣን በሰላም መልቀቃቸው በርካቶችን እያነጋገረ ይገኛል።
በታየ የማመይ ልጅ
18/06/2026
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
S**o
WEE
