Fikir Baye rozi
verse's of counsellor
ያሉኝ ቁሳዊ ስኬቶች ደስታን መስጠት ያቆሙት ለምንድን ነው?
ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ጥልቀት ለሌለው (ቁሳዊ ስኬት) ግዜ እና ሀይላቸውን ከተገቢው በላይ የሚያባክኑ ስዎች ድብርት፣ደስታ ማጣት እናእንደጭንቅት ያሉ ስሜቶችን ማስተናገዳቸው የሚደጋገም ሀቅ መሆኑን ነው።
ለነዚህ ስሜቶች ከሚዳርጉት እንዱ ደግሞ ቁሳዊ ስኬቶችን እንደሁለንተናዊ ስኬት መቁጠርና ትኩረትን+አቅምና ግዜን ስውቶ ከውጤቱ በኃላ ትርጉም ማጣት ነው።
ለዚህ መፍትሄው ቁሳዊ ስኬት ከህይወት ስኬቶች አንዱ እንጂ ሁሉንም አለመሆኑ በመረዳት በመንፈሳዊ፣ማህበራዊ እሴቶች ላይም ጎን ለጎን መስራን ምርጫ ማድረግ ነው።
" ስዎች ራሳቸውን ከባህሪያቸው ይልቅ በስበስቡት ቁሳቁሶች/ምልክቶች መለካት ሲጀምሩ ጥልቀት የሌላቸው ብቻ ሳይሆን አናዳጆችም ስለሚሆኑ ራቅ ማለቱ እና አቅጣጫን መምረጡ ተገቢ ነው"
ማርክ ማንስን
ጤናማ የትዳር ህይወትን ለመምራት ምን ላድርግ?
የትዳር ህይወትን ጤናማ ለማድረግ ቀዳሚው እርምጃ "እያስቡ መኖርን መለማመድ ነው!"
የበርካታ ትዳሮችን የግጭት መንስኤን የመረመሩ ጥናቶች እንደሚያስነብቡት "የዘፈቀደ ንግግር "እና "ግዴለሽነት የተሞላባቸው ድርጊቶች" ዋንኛ የትዳር ጤና ቀውስ ምንጮች መሆናቸውን ነው።
እያስቡ መኖር ማለት "መጨነቅ" አይደለም ትርጉሙ :-"ከግምት ይልቅ መረዳትን ያስቀደመ፣"ጫና ከመፍጠር ወይም በጫና ውስጥ ከመውደቅ ይልቅ ለመታገስ የሚሞክር" ሁሉም ነገር ልክና ያማረ እንዲሆን ከመጠበቅ ይልቅ" የእድገት ሂደት የሆኑትን የየእለት ኑሮ ምስቅልቅሎች በበጎ ዓይን ለማየት መምረጥን የሚያጠቃልል ነው።"
እያሰብክ ለመኖር "ራስህን እና አጋርህን ማክበርና መውደድህ" እንዲህም" በሂደት ውስጥ" የሚገኝን ውጤት መምረጥህ በቂ ነው!!ትርፍህም "ጠንካራ መተማመን"፣"ጥልቅ የሆነ መዋደድ" ከጤናማ የትዳር ህይወት ጋር ይሆናልና መተግበሩ ይመከራል!!
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when Fikir Baye rozi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.