A I For health Sector
Digital health for all Ethiopian
18/08/2026
የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ስብሰባን ለአገር ገፅታ ግንባታ ከማዋል አንጻር የሚድያ ሚና ከፍተኛ ነዉ
__________
ከነሐሴ 16/2018 ጀምሮ አገራችን የምታስተናግደው የ76ኛው የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጠናዊ ስብሰባ (RC76) በማስመልከት ለሚዲያ እና ህዝብ ግንኙነት ባለሙያዎች የግንዛቤ መፍጠሪያ መድረክ በቢሾፍቱ ከተማ ተካህዷል።
የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋሁን ጎበዛይ ስለጉባዔው ግንዛቤ ለመፍጠር እና ለቅድመ ዝግጅቶች የሚደረገው ጥረት የሚበረታታ መሆኑን የገለፁ ሲሆን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ቋንቋዮች የሚሰሩ ሚዲያዎች አጋጣሚውን እንደ ኮንፈረንስ ቱሪዝም እና መልካም ስም መፍጠሪያ ያሉ ጥቅሞችን ግንዛቤ ውስጥ ባስገባ ሁኔታ መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል።
የጤና ሚኒስቴር ህዝብ ግንኙነት እና ጤና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ተገኔ ረጋሳ በበኩላቸዉ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ግዜያት እንደ ወረርሽኝ ያሉ የጤና ስጋቶችን በተቀናጀ ሁኔታ በመረባረብ ውጤቶችን እንዳስመዘገብነው ሁሉ ለአንድ ሳምንት አካባቢ በሚቆየው ይህ ትልቅ ጉባኤ በጤና ጉዳዮች ዙሪያ ከሚደረሱባቸው መግባባቶች እና ውሳኔዎች በተጨማሪ የአገር ገፅታ የሚገነባበት አጋጣሚ በመሆኑ ሁሉም የሚዲያ አውታሮች እና የሚመለከታቸው አካላት በአገራዊ ስሜት ሚናቸውን መወጣት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በአገራችን የአህጉር እና አለም አቀፍ ጉባኤዎችን በስኬት የማስተናገድ አቅም እና ልምድ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተጠቁሟል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V
17/08/2026
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከ278 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የክረምት የጤና በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሰጠ ነው
____
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል በ3 ዞኖች፣ በ22 ወረዳዎች እና በ1 ልዩ ወረዳ ከ278 ሺህ በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ አጠቃላይ የጤና በጎ ፈቃድ አገልግሎት እየተሰጠ ይገኛል።
በበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ከሚሰጡ የጤና ምርመራ አገልግሎቶች:
▪የዓይን እና የጆሮ ሕክምናዎች፣
▪የደም ግፊት፣ የስኳር በሽታ፣ የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር፣ የኤችአይቪ እና የወባ በሽታ ምርመራዎች፤
▪በጤና ተቋም ተገኝተው መታከም የማይችሉ አረጋውያን ላይ ትኩረት ያደረገ የጤና አገልግሎት፤
በክረምት በጎ ፈቃድ ስራዎች 1000 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል።
Website: moh.gov.et
Facebook: Ministry of Health,Ethiopia
Twitter: x.com/fmohealth
YouTube: youtube.com/
Tiktok: tiktok.com/
Telegram: t.me/M0H_EThiopia
Linkedin: lnkd.in/ewFJ6V
15/08/2026
15/08/2026
Building a Resilient Health Economy for East Africa!
Join over 2,000+ delegates, 30+ exhibitors, and leading healthcare decision-makers at the 13th East African Healthcare Federation (EAHF) Conference & Exhibition 2026.
Together with distinguished regional leaders, policy experts, and private sector innovators, we are advancing partnerships, driving innovation, and unlocking investments for a healthier East Africa.
📅 Date: August 21–23, 2026
📍 Venue: Adwa Victory Memorial Museum | Addis Ababa, Ethiopia
Be part of shaping the future of regional healthcare. Save the date!
https://eahf2026.com/public/register.php
Register - EAHF 2026 📢 I am honored to be attending the East African Health Federation – 13th Annual Conference and Exhibition 2026, taking place from August 21–23 at the Adwa Victory Memorial Museum.
12/08/2026
ኢትዮጵያን ከወጣቶቿ ነጥሎ ማየት አይቻልም!
የህዝባችን የእድሜ ስብጥር እንደሚያመላክተው ወጣቶች ከፍተኛውን ቁጥር መያዛቸው፣ ብልጽግናን ለማረጋገጥና ለማፅናትም ታላቅ እድል ነው።
የኢትዮጵያ ወጣት መልካም ዓላማን አንግቦ የሚንቀሳቀስ፣ የለውጥ ዋነኛ ሞተርና የሉዓላዊነታችን ጽኑ ማገር ነው! የኢትዮጵያ ወጣት የሀገሩን ታሪክ በአዲስ ብዕርና ብራና እየጻፈ ይገኛል። ሀገራችንን የኋሊት ጠፍንገው የያዟትን አጓጉል ልማዶች፣ አላስፈላጊ ንትርኮች፣ ጭቅጭቅ እና ግጭቶች በመራቅ የአሁን ወጣት በልማት ላይ አተኩሯል፣ ድህነትን ተጠይፏል።
የመደመር መንግሥት የወጣቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነትና የአመራርነት ሚና ለማጠናከር በትኩረትና በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።
ሀገራዊ ርዕያችንን ዕውን ለማድረግ ሁላችሁም በንቃት እየተጋን፣ በፍቅር እንድንመላለስ ጥሪዬን አቀርባለሁ።
Itoophiyaa dargaggoota ishiirraa adda baasanii ilaaluun hin danda'amu!
Akka umuriin uummata keenyaa mul'isutti dargaggoonni lakkoofsa olaanaa qabachuunsaanii badhaadhina mirkaneessuufi itichuuf carraa guddaadha.
Dargaggoon Itoophiyaa kaayyoo gaarii qabatee kan socho'u, mootora jijjiiramaa adda dureefi dagalee cimaa birmadummaa keenyaati! Dargaggoon Itoophiyaa seenaa biyyasaa qalamaafi waraqaa haaraadhaan barreessaa jira. Dargaggoon ammaa barmaatilee yaraa, walfalmii barbaachisaa hin taane, atakaroofi walittibu'insota biyya keenya takaalanii hidhan irraa fagaachuudhaan misooma irratti xiyyeeffateera; hiyyummaa jibbeera.
Mootummaan Ida'amuu fayyadamtummaa dargaggootaa gama hundaafi gahee gaggeessitummaa isaanii cimsuuf dhimmamee hojjetaa jira.
Mul'ata biyyaalessaa dhugoomsuuf hundi keenyayyuu dammaqinaan cimnee hojjechaa jaalalaan akka deddeebinun waamichakoo dhiyeessa.
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Ababa
3000
