Fedlu Ergicho

Fedlu Ergicho

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Fedlu Ergicho, Health/Beauty, ስልጤ ዞን, Addis Ababa.

28/04/2025

ልብ ሰባሪ ሀዘን አለህ ይዘንልህ

በሰላት የማይደራደረዉ ብርቱ ወንድሜ አሊ ከድር!

ከዉድ ወንድሜ አሊ ከድር ጋር በአካል አንድ ቀን ብቻ ነው የተገናኘነዉ። በስልክ በተለያዩ ጊዜያት ብንወያይም በአንድ ወንድማችን አማካኝነት ከአመት በፊት ተገናኝተን ረዘም ላለ ጊዜያት ወስደን ተወያየን፣ ተነጋገርን።

ወቅቱ ከስልጤ ዞን ሪፎርም፣ እድገትና ልማት ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች በማህበራዊ ሚዲያዎች የበረከቱበት ጊዜ ነበር። በዞኑ የሚከናወኑት የልማት ሪፎርምና ሕዝባችንን ከማርካት አንጻር አናሳ በመሆኑ ጥያቄዎቼን በሶሻል ሚዲያ አማራጮቼ አቀርብ ነበር።

በአካል ለመገናኘት ወሰንና በሁለታችን መሀከል ያለ ወንድማችን በመኖሪያ ቤቱ አወያየን። ትኩረት ሰጥተን በቀጣይ ሪፎርም በሚደረገባቸዉ ቴክኒካዊ ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደረስን። አንዳንድ የአደባባይ ትችቶችን ቀንሰን ዞኑን በሚጠቅሙ ና ይበልጥ በሚያሳድጉ ጉዳዮች ላይ በሕብረት ለመስራት ተስማማን።

ከዛሬ ቡኅላ ትችት አልሰነዝርም አልኩት!

ከወንድሜ አሊ ከድር ጋር በእለቱ ረዘም ላሉ ሰዓቶች እየተወያየን ሳለ በመሀል ሁለት አበይት ነገሮችን አነሳብኝ። እጅግ ትኩረት ሰጠሁት፤ አዉፍም የመባባላችን መቋጫ ሚስጢሩም ይኸው ነዉ።

ይህን ጉዳይ በሕይወት እያለ መፃፍ አለብኝ/የለብኝም ነበር አላውቅም። ነገር ግን አሁን በድንጋጤ ስሜት ዉስጥ ሆኜ ከአመት በላይ የያዝኩትን ጉዳይ ወደሶሻል ሚዲያ አመጣሁት።

ሙጂብ በዞኑ ላይ ችግሮች የሉም ብዬ አልሞግትህም፤ አንዳንዶቹ በራሳችን ችግርና በአቅም ዉስንነት በሌላም በኩል በክልሉ አስተዳዳራዊ ጉዳዮች ይከሰታሉ። እዉነት ነው የስልጤ ዞን በተፈለገዉ መልኩ እድገት አላሳየም። "ሁላችንም የዚሁ ችግር ባለቤቶች ነን" በማለት እንደመሪ ለችግሮች ኅላፊነት በመዉሰድ በቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ለማድረግ ራዕዩን አጋራኝ።

ይቅርታ ተጠያይቀን ፣ ተቃቅፈን የተለያየንበት አጋጣሚ የተፈጠረዉ ወንድሜ አሊ ባስወነጭፋቸዉ ልብ በሚያሞቅ፣ ትሥፋ በሚጭር፣ መተማመንን በሚያጎለብቱ በአጭር አርፍተ ነገሮቹ ነዉ።

እኔ አለ ወንድሜ አሊ- እኔ እንደሌሎች ባለስልጣና ምቾት ላይ ነኝ ብዬ፣ ባለስልጣን ነኝ ብዬ አላህን አላምፅም ቢያንስ ሶላቴን የምስገድ ነኝ አለኝ። በራስ የመተማመኑን ፀዳል ፊቱ ላይ እያነበብኩበት፤ ቀጠለና እንደዘመኑ ባለስልጣናት ሴት የምቀያይር ሳልሆን እምነቴን የምጠብቅ ከእንደዚህ አይነት ነዉር የፀዳዉ ነኝ አለኝ።...

እኔም ተደሰትኩበት፣ ቀጣይ ጥያቄዎቼን ዋጥኳቸዉ፤ ...ብዙ ብዙ ነገሮች በአዕምሮዬ ላይ እየተመላለሱ ተነስቼ አቀፍኩት። ... ይሕን እፁብ ነገር ካሟላ ሌላው ትርፍ ነው ብዬ ለራሴ ነገርኩት...ተደሰትኩበትም: አላህ ይደሰትብህ🤲🏻

አላህ ይማርህ ፤አሏህ በእዝነቱ ይቀበልህ። አላህ ማረፊያህን ጀነተል ፊርደውስ ያድርግል። አሚን! 🤲🏽

Photos from Fedlu Ergicho's post 28/04/2025

ወንድሜ አሊ ከድር
ለሂክማ እስላማዊ ዩኒቨርሲቲ አንተ እና ባልደረቦችህ ያኖራቹትን አሻራ አላህ ይቀበላቹ ዘንድ እየለመንኩ በሂክማ ቦርድ ስም ከልብ የተሰማንን ሀዘን ለመግለጽ እንወዳለን! ሙስሊሙ ኡማም ዱዓ እንዲያድርግለት እጠይቃለሁ 😭😭😭
Redi Sultan

28/04/2025

ኢና ሊላሂ ወኢና ኢለሂ ራጅዑን😭😭😭😭

02/04/2025

መጋቢት 23 ለስልጤ ህዝብ ልዩ መልክት አላት

19/08/2024

ለመኖር ከልካዩ በሰላም ሊኖር👇
የጣምራ ወንጀሎች የለበጣ የፍርድ ዉሳኔ¡
==========================!
"ድሊደግ ተቦዝ በርቼ ሰላም፥ የደበስ የጥራይ"
ይላል የስልጤ ማህበረሰብ።

!

ለአስተያየት እንዲመች ለእያንዳንዱ ወንጀል የተወሰኑ የፍርድ ዉሳኔዎች በዝርዝር
ለ ------ዓመት?
ለ ------ዓመት?
ለ -----ዓመት?
ለ -----------ዓመት?
በድምሩ === #25ዓመት እስራት፥
ፐ! ፐ! ፐ! ፐ! ፐ!
ይህንን የፍርድ ውሳኔ የወሰነው ዳኛ አደንቀዋለሁ፥ ደንዳና ልብ አለው።
እንኳን የህግ ትምህርት አልተማርኩ!
#አልሃምዱሊላህ! ህግ ባለመማሬ ቢያንስ ህሊናዬ ያርፋል።

በህይወት የመኖር መብትን የነፈገ አካል እንዴት ተንደላቆ እንዲኖር ይፈቀድለታል?

መንግስት ሆይ! ግብሩ እና ታክሱ ከፍ በሚለው ልክ የቅጣት ዉሳኔ ለሌሎች አስተማሪ በሚሆን መልኩ እንዲፈፀም በማድረግ ዜጎቻችንን ከጥቃት መከላከል አለብህ።

=======ከድር አወል ነኝ========

Photos from Fedlu Ergicho's post 09/08/2024

ዶክተር እናመሰግናለን!!!

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Addis Ababa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


ስልጤ ዞን
Addis Ababa