Naima Saladin
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Naima Saladin, Health/Beauty, Dire, Addis Ababa.
13/07/2026
በሀረሪ ክልል ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉ ተገለፀ
በሀረሪ ክልል በ2018 የበጀት ዓመት ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉን የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ገልጿል።
የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት መግለጫ ሰጥተዋል።
በመግለጫቸውም መረጃን ለማህበረሰቡ ከማድረስ ባለፈ የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ በማምከን ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች እንዲጠናከር እንዲሁሞ በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦችን እንዲተዋወቁ በማድረግ ረገድ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የተጠናከረ ስራ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።
የክልሉን መልካም ገፅታ በመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎችም በትኩረት ሲከናወኑ መቆየቱንም ገልፀዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በማህበራዊ ሚዲያና በአካባቢው ሚገኙ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎች በመጠቀም ለህዝቡ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።
ከዚህ ባሻገርም የሚዲያ ሞኒተሪንግ፣ የህዝብ አስተያየት ጥናት እና የህትመት ዝግጅትና ስርጭት ስራዎች ላይም ውጤታማ ስራዎች መከናወናቸውን አብራርተዋል።
በወቅታዊ ሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ላይ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ዜናዎች፣ ዶክመንተሪዎች የአቋም መግለጫዎች በማዘጋጀት ለህብረተሰቡ ተደራሽነት ማድረግ መቻሉን ተናግረዋል።
አቶ ሔኖክ አክለውም በተለይም በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማጎልበት ያስቻሉ ስራዎችም ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን ጠቁመዋል።
በሀገራዊ ጉዳዮች ላይም የጋራ መግባባት በመፍጠር ረገድም የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ጥረት ስለመደረጉን አስረድተዋል።
በአዲሱ የበጀት አመትም ተቋሙ የተቋቋመለትን ዓላማ በብቃት እንዲወጣ ለማስቻልና የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰራ ነው ኃላፊው የተናገሩት።
13/07/2026
በሀረሪ ክልል ወቅቱን የዋጀ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ
አዲስ አበባ ፤ ሐምሌ 6/2018 (ኢዜአ) ፦ በሀረሪ ክልል ወቅቱን የዋጀ የሚዲያና የኮሙኒኬሽን ተግባራትን አጠናክረን እንቀጥላለን ሲል የክልሉ መንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።
የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ ሔኖክ ሙሉነህ በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የተከናወኑ ተግባራትን በሚመለከት በሰጡት መግለጫ መረጃን ለማህበረሰቡ ከማድረስ ባለፈ የአፍራሽ ሀይሉን አጀንዳ በማምከን ረገድ አበረታች ስራዎች መከናወናቸውን ተናግረዋል።
ጽሕፈት ቤቱ በክልሉ በ2018 የበጀት ዓመት ወቅቱን የዋጀ የኮሙኒኬሽንና የሚዲያ ተግባራትን ማከናውን መቻሉንም ገልጸዋል።
የክልሉ ህዝብ በሰላም፣ በመቻቻልና በአብሮነት የመኖር እሴቶች እንዲጠናከር እንዲሁሞ በክልሉ የሚገኙ የቱሪስት መስህቦች እንዲተዋወቁ በማድረግ ረገድ የተለያዩ የሚዲያ አውታሮችን በመጠቀም የተጠናከረ ስራ ሲሰራ መቆየቱንም ገልጸዋል።
የክልሉን መልካም ገፅታ በመገንባት በህዝብና በመንግስት መካከል ሁነኛ የመረጃ ድልድይ ሆኖ ተግባቦትን የመፍጠር ስራዎችም በትኩረት ሲከናወኑ መቆየታቸውንም አስረድተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ የሚከናወኑ የልማትና መልካም አስተዳደር ስራዎችን በማህበራዊ ሚዲያና በአካባቢው የሚገኙ ሀገር አቀፍ ሚዲያዎችን በመጠቀም ለህዝቡ ተደራሽ ተደርጓል ብለዋል።
አቶ ሔኖክ አክለውም በተለይም በክልላዊና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ የህብረተሰቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማጎልበት ያስቻሉ ስራዎችም ትኩረት ተሰጥቶት መሰራቱን ጠቁመዋል።
የጋራ መግባባት በመፍጠር ረገድም የኮሙዩኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን እንዲወጣ ለማስቻል ጥረት ስለመደረጉም አስረድተዋል።
በአዲሱ የበጀት አመትም ጽሕፈት ቤቱ የህብረተሰቡን የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት በትኩረት እንደሚሰራ ነው ኃላፊው የተናገሩት።
Ethiopian News Agency #ኢዜአ
13/07/2026
ተስፉን እንትከል!
"ዛሬ የምናሳርፈው አረንጓዴ አሻራ፣ የነገው ብልፅግናችን ዋስትና ነው!"
13/07/2026
#ኢትዮጵያ እየመከረች ነው
በመጪው ሐምሌ 8 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለሚካሄደው የሀገራዊ ምክክር ጉባኤ 2 ቀን ቀረው!
13/07/2026
"አቅመ ደካማ እናቶችን መደገፍ የልመና ማቆሚያ፣ የክብር ማረጋገጫ መንገዳችን ነው!"
13/07/2026
ሳምንታዊ መልዕክት
አረንጓዴ አሻራ የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ብልፅግና በጽኑ መሠረት ላይ የሚገነባ የትውልድ አሻራ ነው!
አለማችን በከባድ የአየር ንብረት መዛባት ምክንያት በጎርፍና ድርቅ እየተፈተነች ባለችበትና ለችግሩ በተግባር የተደገፍ በቂ ትኩረትና መፍትሔ ባልተሰጠበት አስቸጋሪ ወቅት የሰዉ ዘር መገኛ የሆነችዉ ኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን እንደ መፍትሄ ይዛ ተከሰተች።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በ2011 ዓ.ም በፓርቲያችን ፕሬዚዳንት ክቡር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የተጀመረ ትልቅ ሀገራዊ ኢኒሼቲቭ ሲሆን፤ አላማዉም የኢትዮጵያና ህዝቦቿን ሁለንተናዊ ብልፅግናን እዉን የማድረግ ሂደት ዉስጥ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥና የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚ የመገንባት ራዕያችን አካል ነዉ።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር በ2011 ዓ.ም ለሰፊዉ ህዝብ ከተበሰረ እለት ጀምሮ እስከ 2017 ዓ.ም ድረስ በታላቅ ህዝባዊ ንቅናቄ በፖለቲካ አመለካከት፣ በቋንቋ፣ በባህል፣ በሃይማኖት፣ በብሔር፣ በፆታ ሳንለያይ ከህፃናት እስከ አረጋዊያን፣ ከወጣቶች እስከ እናቶች/አባቶች ሁላችንም በአንድነትና በተባበረ ክንድ ዘርፈ ብዙ ጥቅም ያላቸዉ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል እንደ ትዉልድ አዲስ ታሪክ አስመዝግበናል።
ከዛም ባለፈ በአንድ ጀምበር ከ700 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን በመትከል አለማቀፍ ሪከርዶችን በመስበር ጭምር ልክ እንደ አድዋ ድል የኢትዮጵያውያን የማሸነፍ እና የመቻል አቅም ለመላዉ አለም አሳይተናል።
የግብርና ሚኒስትር መረጃ እንደሚያመለክተው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር ከመጀመሩ በፊት የሀገራችን የደን ሽፋን 17.2 በመቶ አካባቢ የነበር ሲሆን፤ በተከታታይ በተደረጉ የችግኝ ተከላና እንክብካቤ ስራዎች የሀገራችን የደን ሽፋን አሁን ላይ ወደ 23.6 በመቶ አድጓል።
በሌላ በኩል በጥቂት ዓመታት ዉስጥ የምንተክላቸዉን ችግኞች ቁጥር ወደ 65 ቢሊዮን ከፍ በማድረግ የሀገራችን የደን ሽፋን ወደ 30 በመቶ ለማሳደግ ትልቅ ሀገራዊ ራዕይ ስንቀን ወደ ፊት እየገሰገስን እንገኛለን።
ባለፉት ሰባት ዓመታት የተተከሉት በቢሊዮን የሚቆጠሩ እንደ አቮካዶ፣ ማንጎ፣ፓፓያ፣ ቡናና የመሳሰሉት ችግኞች የዜጎችን የምግብ ዋስትና ከማረጋገጥ ባለፈ፣ ለአገር ውስጥ ገበያ እና ለውጭ ኤክስፖርት ትልቅ አቅም እየሆኑ መተዋል።
እንደ ምሳሌም ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 30ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ሪፖርት ሲያቀርቡ "ኢትዮጵያ 2018 ዓ.ም ብቻ ከቡና ምርት 3.1 ቢሊዮን ዶላር ገቢ አግኝታለች። ባለፉት 17 ዓመታት ውስጥ ከተገኘው 3.3 ቢሊዮን ዶላር ጋር ሊስተካከል ተቃርቧል። የዘንድሮው ገቢ ከአፍሪካ 1ኛ፣ ከዓለም ደግሞ 3ኛ ነው። ይህ የሪፎርም እና የአረንጓዴ አሻራ ውጤት ነው” ብለዉ መግለፃቸው ይታወሳል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብርን ከስራ እድል ፈጠራ አንፃር ስናየዉ ጥቅሙ የእትዬ ለሌ ነዉ፤ በመላዉ ሀገሪቱ ከ120,000 በላይ የችግኝ ጣቢያዎች ዉስጥ ከ767,000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድሎችን መፍጠር መቻሉን እና ከእነዚህም ውስጥ አብዛኛዎቹ ሴቶች እና ወጣቶች መሆናቸዉን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ዉድ ኢትዮጵያውያን አረንጓዴ አሻራችንን ስናኖር የምንተክለዉ ዛፍ ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱ ተክል ነገ አድጎ የገቢ ምንጭና የምግብ ዋስትናችን በመሆኑ ከኛም አልፎ ለልጆቻችን የሚተርፈዉን የእለት ምግባችንን ዛሬ እንትከል።
በእጃችን የምንተክለዉ ዛፍ አለምን በከፍተኛ ሁኔታ እየተነ ያለዉን የአየር ንብረት መዛባት ድርቅና ጎርፍን የምንዋጋበት አስተማማኝ መሳሪያና መጠለያ ስለሆነ ነገ ልጆቻችን የሚጠለሉበትን ጥላና የሚተነፍሱትን ንፁህ አየር ዛሬዉኑ እንትከልላቸዉ።
አሻራችንን ስናኖር ሁሉን አብቃይ ለም የተፈጥሮ አፈራችንን እየተንከባከብንና እየጠበቅን በመሆኑ የአፈር መሸርሸርን በመከላከል መሬታችን ለምነቱን ጠብቆ ምርትና ምርታማነት እንዲጨምርና የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ጉዟችን በአጭር ጊዜ እንዲሰምር ዛሬዉኑ ዛፍ በመትከል አሻራችንን ለትዉልድ እናኑር።
ዛሬ የምንተክለዉ ትንሽዬ ችግኝ የከርሰ ምድር ውሃን የምንቆጥብበትና ለሰዎች፣ ለእንሰሳት፣ ለዱር አራዊት፣ ለእፅዋት እና ለሁሉም ፍጡር ንፁህ የተፈጥሮ ምንጭ ዉሃን ከተራሮቻችን ስር ለማፍለቅ ዛሬ ችግኝ እንትከል፤ የተከልነዉን ተንከባክበን ለታለመለት አላማ እናዉል።
ባለፉት 7 አመታት በአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር የተገኙትን ዘርፈ ብዙ ስኬቶችን ለማስቀጠል የዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሃግብር "ተስፋን እንትከል" በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ 8 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ በመላዉ ሀገሪቱ ሰፊ ህዝባዊ ንቅናቄ እየተካሄደ ይገኛል።
በዘንድሮዉ መርሃግብር ከሚተከሉ ችግኞች መካከል 40 በመቶው ሀገር በቀል የደን ዛፎች ላይ ትኩረት ሲደረግ 60 በመቶው ደግሞ ለምግብ ዋስትናና ለሌሎች ዘርፈ ብዙ ጥቅሞች የሚውሉ የፍራፍሬና የኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች መሆናቸውን ከግብርና ሚኒስትር የተገኘዉ መረጃ ያመልክታል።
ዉድ ኢትዮጵያዊያን ዛሬ በእጃችሁ የምትተክሉት ችግኝ በሁሉም ዘርፍ የበለፀገች፣ ልጆቿ ደስተኛ ሆነዉ በምቾት የሚኖሩባት፣ ከራሷ አልፋ ለሌሎች የምትተርፍ ታላቋን የነገዋን ኢትዮጵያ መገንባት ነዉና ይህን የክረምት ወቅት ሳናባክን በአግባቡ እንጠቀምበት። በእጃችን ሀገራችንን እንገንባ፤ ለመጪው ትውልድ ተስፋን በመትከል ታሪካዊ አሻራችንን እናኑር!
ብልፅግና ፓርቲ
ሀምሌ 6, 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ
13/07/2026
12/07/2026
በሀረሪ ክልል በ2018 በጀት አመት በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገለፀ
በክልሉ በ2018 በጀት አመት በጤናው ዘርፍ አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን የክልሉ ጤና ቢሮ ገልጻል።
የሀረሪ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶ/ር አብዲ አሚን በቢሮው በ2018 በጀት አመት በተከናወኑ ስራዎች ዙሪያ መግለጫ ተጥተዋል።
የቢሮው ኃላፊው በሰጡት መግለጫ የጤና አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራትን ለማሳደግ በተከናወኑ ስራዎች አበረታች ውጤቶች መገኘታቸው ገልጸዋል።
በ2018 በክልሉ ውስጥ በሚገኙ የጤና ተቋማት ከ 1 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በተመላላሽ ህክምና አገልግሎት ማግኘታቸውን ገልፀዋል።
በክልሉ በ2018 የበጀት አመት ጥራት ያለው የህክምና አገልግሎት ለማህበረሰቡ ተደራሽ ለማድረግ የተከናወኑ ስራዎች ተጨባጭ ውጤት አስገኝቷል ብለዋል።
ተላላፊና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከልና በማከም ረገድም የተሰሩ ስራዎችም አበረታች ውጤቶች መመዝገባቸውን ገልጸዋል።
ለእናቶችና ህፃናት ጤና እንዲሁም ለማህፀን በር ካንሰር፣ ለስኳርና ለደም ግፊት የቅድመ ምርመራና ህክምና ስራዎች ትኩረት በመስጠት መሰራት መቻሉን ጠቁመዋል።
ሀረር ከተማን የሜዲካል ቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑ የገለጹት ኃላፊው በተለይም የግሉ የጤና ዘርፍም በዚህ ረገድ ሚናውን እንዲወጣ ተገቢ አመራር እየተሰጠ እንደሆነ ጠቁመዋል።
በተለይም በ2018 የጤና መድህን የአባላት እድሳትና ምዝገባ 35 ሺህ 245 አባ/እማ ወራን በመዝገብ የአባላት የእድሳት ምጣኔውን 100% ማድረስ የተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
በክልሉ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን አገልግሎት ሽፋን ከመጨመር ባለፈ የአገልግሎቱ ተጠቃሚዎች የተሟላ አገልግሎት እንዲያገኙም የላቀ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራ መቆየቱን አብራርተዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በክልሉ በማህበረሰብ አቀፍ የጤና መድህን ስራ እንደሀገር በምሳሌነት የሚጠቀስ ውጤት መመዝገቡን ነው የገለፁት።
ከዚህ ባሻገር የጤና መሰረተ ልማት በማስፋፋት ረገድም ልዩ ትኩረት በመስጠት በገጠር ወረዳዎች አዲስ ኮምፕሬሲቭ ሄልዝ ፖስት መገንባቱን ገልጸው አዲስ ሆስፒታል እና ኮምፕሬሲቭ ሄልዝ ፖስት ግንባታ መጀመሩን ገልጸዋል።
የሪጅናል ላብራቶሪ እና የተሃድሶ ህክምና ማዕከል ተመርቆ ስራ መጀመሩና ከዚህ በተጨማሪም ሁለት ጤና ጣቢያዎች እድሳት መካሄዱን ገልጸዋል።
የግል ጤና ተቋማትን በመደገፍና ተገቢውን ክትትትል በማድረግ የህዝብን የጤና አገልግሎትና ተደራሽነት እንዲሰፋ መሰራቱን ገልጸዋል።
በቀጣይ የበጀት ዓመትም የተገኙ ውጤቶችን በማጠናከር እየጨመረ የሚገኘው የህብረተሰቡን የጤና ፍላጎት ለማርካት የሚችል የጤናው ዘርፍ የ2019 እቅድን ለመፈፀም በቁርጠኝነት ይሰራል ብለዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Dire
Addis Ababa
