Hussen Haji Ibrahim

Hussen Haji Ibrahim

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hussen Haji Ibrahim, Health/Beauty, Alaba K'ulito.

26/07/2026

Halaabi xooggatu K'uufe k'abaleeni kabare hoshshaani baadi dudubu xaaxak'k'amani

25/07/2026

በሀላባ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት የአስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል መሪ ቃል የ2018/2019 ዓ.ም በክረምት ወራት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ለአቅመ ደከመ ቤት ለማስገንባት ተግባሩን በይፋ ጀመረ

በዚህም የዞኑ አስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት ውስጧ ያሉ ቤተሰቦቿን አባላትን ሙሉ አቅም በማሳተፍ በዞኑ ዌራ ወረዳ በላይኛው ሌንዳ ቀበሌ ለአንድ አቅመ ደካማ ቤተሰብ የቤት ግንባታ የሚሆን ቆርቆሮና ምስማር ድጋፍ በማድረግ ተግባሩን በይፋ አስጀምረዋል።

በዚህ ወቅት ተግባሩን በይፋ ያስጀመሩት የሀላባ ዞን ፐብሊክ ሰርቭስና ሰው ሀብት ልማት መምሪያ ሀላፊ እና የዞኑ አስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት ምክትል ሰብሳቢ
አቶ አበበ አሊዬ የአቅመ ደካማ ቤቶች ግንባታው በዞኑ አስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት ባሏት ቤተሰቦቿ አባላት በበጎ ፍቃድ ተግባር እንደሚከናወኑ ገልጸዋል።

በዚህም በዞኑ ዌራ ወረዳ በላይኛው ሌንዳ ቀበሌ በፍትህ ብልጽግና ቤተሰብ አማካኝነት የተጀመረውን ጨምሮ በ3 ቀበሌያት መቃለ ሀ እና፣አሶሬ ቀበሌያት ለሚገኙ ለሶስት አቅመ ደከሞች ቤት ለማስገንባት ተግባሩን በይፋ ተጀምሯል ብለዋል።

የህብረቷ አባላት የሚያገኙት ገቢ ከራሳቸው ተርፎአቸው ሳይሆን የብልጽግና ፓርቲ እሳቤን ወደተግባር በመቀየር
ከራሳቸው ይልቅ የእኛን ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን እንደግፍ በሚል ለአቅመ ደከሞቹ ቤት ለመገንባት መነሳሳታቸውንና
በተለይም በፋብሪካ ቁሳቁሶችና የቤት ገንቢ ሠራተኞች ብር በመክፈል እና ቀበሌያቱ ማህበረሰብን በማሳተፍ ጭቃ እንደሚለጥፉ አብራርተው ለተግባራዊነቱ የበኩላቸውን እንዲወጡ አቶ አበበ አሳስበዋል ።

በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የሀላባ ዞን ምክር ምክትል አፈጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ረውዳ ዘይኔ ባስተላለፉት መልእክት የዞኑ አስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት "በጎነት ለኢትዮጵያ ከፍታ"በሚል የጀመረው ይህ ተግባር ፓርቲያችን ሰው ተኮር መሆኑን በውል ያረጋገጠ ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም የቤቶቹ ግንባታ ተጠናቆ ቁልፍ ርክክብ እስኪፈጸም ድረስ ሁሉም በትብብር እና በቅንጅት መስራት እንደሚጠበቅባቸው ምክትል አፈጉባኤዋ አሳስበዋል።

አቶ ገረሙ ሱኒኪቻ የሀላባ ዞን ፍትህ መምሪያ ሀላፊና የፍትህ ቤተሰብ ሰብሳቢ በበኩላቸው መሰል የበጎ ተግባራት የህዝብ ለህዝብ ትስስር የሚያጠናክሩበት እና ለ ለችግር የተገለጡ ወገኖቻችንን የመደገፉ በጎ ተግባር በቀጣይነት ባህል ልናደርግ ይገባል ብለዋል።

በዚህም ፍትህ ቤተሰብ አባላት እና ባለድርሻ አካላት በተቀናጀ ተሳትፎ በዛሬው እለት የተጀመረውን የቤት ግንባታ በጥራት በመገንባት ፈጥኖ በማጠናቀቅ ቁልፍ ርክክብ ለማድረግ በአጽንኦት እንደሚሠሩ አቶ ገረሙ ተናግሯል።

በፕሮግራሙ ላይ የዞኑ አስተዳደር ዘርፍ ብልጽግና ህብረት አመራሮችና አባላትና ህብረቷን ደጋፊ ኮማንድፖስት ተገኝተዋል።
ሲል የሀላባ ዞን ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽህፈት ቤት ሚዲያና ኮሙኒኬሽን ዘርፍ ዘግቧል።

Photos from የሀላባ ዞን መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ's post 08/07/2026
Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Alaba K'ulito?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Alaba K'ulito