Abu amiralmuminin

Abu amiralmuminin

Share

Support macro business

14/06/2026

የአትላስ አንበሶቹ ብራዚልን አስጨንቀው አመሹ::

ጨዋታው በአስደናቂ አቻ ውጤት ተጠናቋል

ያለ እንቅልፍ ያሳለፉትን ምሽት ሙሉ በሙሉ የሚያስቆጭ ድንቅ እግር ኳስ በሞሮኮ እና በብራዚል ብሔራዊ ቡድኖች መካከል ተካሂዶ በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው ይህ ጨዋታ እጅግ ማራኪ፣ ፈጣን እና የሞሮኮን እግር ኳስ እድገት ዳግም በዓለም መድረክ ላይ ያስመሰከረ ሆኖ አልፏል።

በጨዋታው መጀመሪያ ላይ ሞሮኮዎች ያሳዩትን ፍፁም የበላይነት ወደ ግብ በመቀየር በ21ኛው ደቂቃ ላይ ኢስማኤል ሳይባሪ አስደናቂ ግብ አስቆጥሮ ሀገሩን ቀዳሚ ማድረግ ችሎ ነበር።

ሆኖም ግን የብራዚሉ እውቅ ኮከብ ቪኒሲየስ ጁኒየር በ32ኛው ደቂቃ ላይ ለካናሪዎቹ የአቻነቷን ግብ በማስቆጠር ጨዋታውን ወደ መጀመሪያው ሚዛን መልሶታል።

ምንም እንኳ ጨዋታው በ1 ለ 1 አቻ ውጤት ቢጠናቀቅም የዕለቱ እውነተኛ ኮከብ ግን ሞሮኮ ነበረች ማለት ይቻላል።

በተለይም በመጀመሪያው አጋማሽ ሜዳውን ሙሉ በሙሉ በመቆጣጠር ለዓለም ኃያሏ ብራዚል ከባድ ፈተና ሆነው ያመሹት የአትላስ አንበሶቹ ለአፍሪካ እግር ኳስ ትልቅ ኩራት የሆነ ምሽትን አሳልፈዋል።

ጨዋታው በእውነትም እንቅልፍ አጥቶ ለመከታተል የሚገባ አስደናቂ ፍልሚያ ነበር።

እናንተስ በሞሮኮ አስደናቂ ብቃት ምን ያህል ተደንቃችኋል?

ጨዋታውንስ እንዴት አገኛችሁት?

የእናንተን አስተያየት በኮሜንት መስጫው ላይ ያጋሩን።

⚽️⚽️⚽️

13/06/2026

ኢላህ አንተ ተውቃለህ 🙏

13/06/2026
Photos from Abu amiralmuminin's post 13/06/2026

የኢራን ብሔራዊ ቡድን ለሚናብ ህጻናት ያደረገው ልብ የሚነካ መታሰቢያ መነጋገሪያ ሲሆን የዘንድሮው የአለም ዋንጫ የእስራኤል መንግስት በግልጽ የተወገዘበት መድረክ ሆኗል

በ2026ቱ የፊፋ አለም ዋንጫ ዋዜማ፣ የኢራን ብሔራዊ የእግር ኳስ ቡድን በቅርቡ በሚናብ ከተማ በተፈጸመው ጥቃት ህይወታቸውን ላጡ ከ165 በላይ ንጹሃን ህጻናት ልብ የሚነካ የክብር መታሰቢያ አድርጓል። ይህ ተግባር የዘንድሮውን የአለም ዋንጫ ከስፖርታዊ ውድድርነት ባለፈ፣ የእስራኤል መንግስት እና የአሜሪካ የጦርነት ፖሊሲ በአለም አቀፍ ደረጃ በግልጽ የሚወገዙበት መድረክ አድርጎታል።

የኢራን ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾች ከናይጄሪያ እና ከኮስታሪካ ጋር ባደረጓቸው የቅድመ-አለም ዋንጫ የወዳጅነት ጨዋታዎች ላይ የህጻናቱን መታሰቢያ በልዩ ሁኔታ ዘክረዋል፡ የቡድኑ አባላት የህጻናቱን የትምህርት ቤት ቦርሳዎች ደረታቸው ላይ አቅፈው ለብሔራዊ መዝሙር ቆመዋል። በሌላ መርሃግብር ላይ ደግሞ በአሜሪካ እና እስራኤል ጥቃት ህይወታቸው ያለፈውን የሰማዕታት ህጻናት ፎቶግራፎች ይዘው በመውጣት ሀዘናቸውን በአደባባይ ገልጸዋል። በውድድሩ ላይ የሚሳተፈው የኢራን የልዑካን ቡድን የህጻናቱን ትውስታ ዘላለማዊ ለማድረግ "ሚናብ 168" በሚል ስያሜ ወደ ውድድሩ እንደሚያቀና አረጋግጧል።

ይህ በአሜሪካ፣ ካናዳ እና ሜክሲኮ አስተናጋጅነት የሚካሄደው የ2026 የአለም ዋንጫ የተለየ ፖለቲካዊ እና ሰብአዊ ትርጉም ይዟል። የኢራን ብሔራዊ ቡድን ያሳየው አቋም፣ ስፖርታዊ መድረኮች የእስራኤል መንግስት በንጹሃን ላይ እያደረሰ ያለውን ጥቃት ለማጋለጥ እና በአለም አቀፍ ደረጃ ለማውገዝ እንዴት ጥቅም ላይ ሊውሉ እንደሚችሉ በግልጽ አሳይቷል።

የእስራኤል መንግስት እርምጃዎች በዚህ ልክ በአለም አቀፍ የስፖርት መድረክ ላይ በግልጽ ሲወገዙ ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ሲሆን፣ የኢራን ብሔራዊ ቡድን ያቀረበው ይፋዊ ተቃውሞ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የስፖርት አፍቃሪያንን ቀልብ ወደ ቀጠናው ሰብአዊ ቀውስ እንዲስብ አድርጎታል። እንደ ፕሬስ ቲቪ ዘገባ፣ ይህ ክስተት የእስራኤልን የጦር ወንጀሎች በአለም አደባባይ እርቃኑን ያስቀረ እና ለተጎጂዎች ትልቅ የሞራል ድጋፍ የሰጠ ታሪካዊ አጋጣሚ ሆኖ ተመዝግቧል።

በመሐመድ ሚፍታህ ደርብ

Photos from Abu amiralmuminin's post 12/06/2026

የአሚን ሆስፒታል ባለቤት ዶክተር መሀመድ ሽኩር ለሀላባ ከነማ ድጋፍ ለማድረግ ቃል የገቡትን 2,000,000 ብር ገቢ አደረጉ!

የሀላባ ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በመግባቱ የተሰማቸውን ደስታ በመግለፅ 2,000,000 ብር ድጋፍ ለማድረግ ቃል መግባታቸው ይታወሳል።

ዶክተር መሀመድ የገቡትን ቃል ወደ ተግባራዊ አድርገዋል ከልብ እናመሰግናለን!!!

11/06/2026

በሳዑዲ ዐረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1 ሺሕ 655 ኢትዮጵያውያን የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምሕረት አዋጅ እንዲሰጣቸው ተደርጓል - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሪያድ የሚገኘውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮን እና ጂዳ የሚገኘውን ቆንስላ ጽ/ቤት በማስተባበር በተደረገ የዲፕሎማሲ ጥረት በሳዑዲ ዐረቢያ ለእስር ተዳርገው የነበሩ 1 ሺሕ 655 ዜጎች የፍርድ ሂደታቸው ተቋርጦ የምሕረት አዋጅ እንዲሰጣቸው መደረጉን አስታውቋል፡፡ ሚኒስቴሩ ይህን ያሳወቀው ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 4/2018 ባሰራጨው አጭር መረጃ ነው፡፡

ሚኒስቴሩ ይህ ውጤት መንግሥት በውጭ ግንኙነቱ ለዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሰጠው ትኩረት የተገኘ ነው ብሏል፡፡ ከዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ አኳያ በሳዑዲ አረቢያ ቀሪ የዲፕሎማሲ ጥረት የሚሹ ጉዳዮችን በተመለከተም ክትትል እያደረገ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

አያይዞም መንግሥት ኅብረተሰቡ ከሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በማኅበራዊ ሚዲያ የታጀበ ሐሰተኛ ማታለያ ድርጊት የውጭ ሀገር ጉዞ ራሱን እንዲጠብቅ ያሳሰበ ሲሆን፤ ሕገ ወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎችን የሕግ ተጠያቂ ለማድረግ የተጀመሩ ጥረቶች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ማረጋገጫ ሰጥቷል። (ሚንበር ቲቪ)

25/05/2026

አንዘንጋ በረከለሁፊኩም 🙏🙏🙏

16/05/2026

ይደረግ 🙏

16/05/2026

የአስቸኳይ የጥቆማ ማስታወቂያ፡ የጠፋች ህፃን ለቤተሰቦቿ እናድርስ።
በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 ልዩ ቦታው ታቦት ማደሪያው ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አንዲት ህፃን ተገኝታለች። ህፃኗ በአሁኑ ሰዓት በእንጅባራ ከተማ ቀበሌ 05 አስተዳደር ጥበቃ ስር ትገኛለች።

የዚች ህፃን ቤተሰቦች፣ ዘመዶች ወይም ህፃኗን የምታውቁ ነዋሪዎች ካላችሁ በአስቸኳይ ቀበሌ 05 ጽህፈት ቤት በመገኘት እንድትረከቡ እናሳስባለን።

ይህንን መረጃ የምታነቡ የከተማችን ነዋሪዎች፣ ህፃኗን ለቤተሰቦቿ ለማድረስ እንዲቻል ይህንን መረጃ ሼር (Share) በማድረግ ተባበሩን።

“አንድነትና መረዳዳት ለህፃናት ደህንነት!”

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Butajira?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Telephone

Website

Address


Butajira
WORABE