Ginba great
I want to know the truth source
ትግስትን በመከራ ጊዜ ማሳለፍ ከጥበብም በላይ ጥበብ ነዉ ።ጥበብን መማር የሚቻለዉ ት/ቤት ገብቶ ፊደል ቆጥሮ ቢሆን ኑሮ ስንቶቻችንን ነን የዚህ እድል ተጠቃሚ የምንሆነዉ ?ስለዚህ ወዳጄ ሆይ ጥበብን ለመማር ከምታየዉ እና ከሚደርስብህ ነገር ተማር ።ያለበለዚያ የጥበብ ድሀ ትሆናለህ ።አንዱ የጥበብ ማዛያ ዘዴ ትግስት ነዉ ። ትግስት እንዴት የጥበብ መማሪያ ሊሆን ይችላል ?ብለህ ልጠይቅ ትችላለህ ።ትግስትን ልትማርና ጥበብ መሆኑን የምታቀዉ በሚደርሱብህ ችግሮችና የመከራ ስአት ነዉ ። ለምሳሌ ስትራብ ፣ስትታረዝ ፣ስትሸነፍ ፣ስታፈቅር ፣ስታዘን ያኔ አንተም ምንም አይነት ሀይል እንደለለህ ታዉቃለህ ።ያን ኩሉ ያሳለፍከዉ በትግስት መሆኑን ኃላ ያሁሉ አልፎ እንደቀልድ ስታየዉና ስታወራዉ ለካ ይህ ሁሉ ነገር ያለፈዉ በመታገሴ ነዉ ብለህ ማሰብ ትጀምራለህ ።እና ታዳ ጥበብ ማለት ይህ አይደል እንዴ !!አየህ አይደል ጥበብ የሚመጣዉ በመማር ብቻ ሳይሆን በሚደርሱብህ መከራና ችገር መሆኑን ተረዳህ ።
20/08/2022
አስተዉል
ትንንሽ ቁልፎች ትልልቅ በሮችን ይከፍታሉ ።
ትንንሽ ቃላቶች ትልልቅ ኣላማን ያፈረሳሉ ።
ትንንሽ ሀሳቦች ትልቅ አቅምን ይገነባሉ ።
ትንንሽ ፈተናዎች ትልቅ አላማዎችን ያሳካሉ ። ስለዚህ ትነንንሽ ነገሮችን ሳትንቅ በሚያጋጥሙህ መሰናክሎች ተስፋህን አታጨልም ያለ ትንሽ ትልቅ መሆን ስለማይቻል ። ታላቅ ለመሆን ታንሽን አክብር ።
እንኳን ለቡሄ በአለም በሰላም አደረሰን
ባአሉ የሰላም የደስታ ያድርግልን ።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Website
Address
Ginba
Dessie
