Hassen seid
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Hassen seid, Health/Beauty, Gondar.
24/10/2024
07/09/2021
#ጭና!
የአሸባሪ ቡድኑ የበቀል ዱላ ያረፈባት፤
የሃይማኖት አባቶች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ህጻናትና እናቶች የተገደሉባት፣
የጅምላ ግድያ የተፈጸመባት፤
ደባርቅ፡ ጳጉሜን 02/2013 ዓ.ም
(የሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን)
#በሰሜን ጎንደር ዞን #ዳባት ወረዳ ጭና ቀበሌ የትግራይ ወራሪ ሃይል ዳባትና ደባርቅን ለመቆጣጠር ቢፈልግም፤ ከሰራዊታችን ባሻገር በደባርቅና በዳባት ወጣቶች ከፍተኛ ተጋድሎ የቅዠት ህልሙ ተጨናግፎበታል፤ በጭና ምድር ወራሪ ሃይሉ ከፍተኛ ቁሳዊና ሰብኣዊ ኪሳራ ደርሶበታል፡፡
በጭና የእርሻ ማሳዎች፣ በጎዳናዎችና በአርሶ አደሮች ቤት የወራሪ ሃይሉ አባላት የቄጤማ ያህል ተነስንሰዋል፡፡ ይህ ድርጊት ያሳፈረዉ ወራሪ ቡድን በጭና ንጹሃን ላይ የበቀል ዱላዉን አሳርፏል፡፡ ካህናት፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ህጻናት፣ ወጣቶችና እናቶች የግፉ ሰለባ ሆነዋል፡፡
ከአንድ ቤተሰብ እስከ 6 አባላት ተሰዉተዋል፤ በየቦታዉ ከ40 እስከ 50 የሚጠጋ የንጹኃን አስከሬን ተገኝቷል፤ አሁንም ድረስ ምናቸዉም ያልተገኙና ደብዛቸዉ የጠፉ ንጹሃን በርካታ ናቸዉ፤ ቤተሰቦቻቸዉ ፍለጋ ላይ ናቸዉ፡፡ በህይዎት የተረፉትም ቢሆኑ በአካባቢዉ ያልተቀበረዉ የጠላት አስከሬን በፈጠረዉ መጥፎ ጠረን ተረብሸዉ ቤታቸዉን ጥለዉ ለመዉጣት ተገደዋል፡፡
"ከእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉ" አበዉ ቤተሰቦቻቸዉን፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸዉን በግፍ ያጡት የአካባቢዉ ነዋሪዎች ሃዘናቸዉን በቤታቸዉ እንዳያሳልፉ የጠላት አስከሬን አለመነሳት ማህበራዊ ረፍት ነስቷቸዋል፡፡
በርካታ ንጹሃን በግፍ የተገደሉባት ጭና በደም ታጥባለች፤ ጎዳናዎቿ በሬሳ ጠረን ከርፍተዋል፤ አስቸኳይ እገዛን ይሻሉ፤ ሁሉም ፊቱን ወደ ጭና ሊያዞር ይገባል፤ ጭና የግፍ ጽዋን ከተጎነጩ የአማራ አካባቢዎች አንዷ ሆናለች፤ የጭና ወገኖቻችን የቤት እቃቸዉ፣ ሃብት ንብረቶቻቸዉ ተወስዶባቸዋል፤ እናት ልጅ አልባ፣ ልጆች ወላጅ አልባ ሆነዋል፤ የጭና ወገኖቻችን ጭንቅ ላይ ናቸዉ፡፡ ፈጥነን እንድረስላቸዉ!!
#ፈንታ ተረፈ (ከግንባር ቀጠና)
ተጨማሪ መረጃዎችን ከሰሜን ጎንደር ኮሙዩኒኬሽን የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፦
በቴሌግራም፦https://t.me/joinchat/qiaYdjh7C40zMjA8
በዩቱብ፦https://youth.be/91mW50wGJc
Hassen seid Send a message to learn more
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Telephone
Website
Address
Gondar
