FiiRii Michael
ilmaa sabaa
21/07/2026
ፕሮጀክቱ ሀረርን የምሥራቅ ኢትዮጵያ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል ስትራቴጂያዊ እርምጃ ነው-አቶ ሔኖክ ሙሉነህ
ሀረር፣ሀምሌ 14/2018(ሀክመኮ):- የሀረሪ ክልል የአየር ማረፊያ ፕሮጀክት ሀረርን ምሥራቅ ኢትዮጵያ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል ስትራቴጂያዊ እርምጃ መሆኑን የክልሉ መንግሰት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤት ሀላፊ አቶ ሔኖክ ሙሉነህ ገለፁ።
እንደ ሀላፊው ገለፃ ሀረር በዩኒስኮ የተመዘገቡ ሁለት ቀርሶችን ጨምሮ በርካታ ቀሳዊና መንፈሳዊ ቅርሶች መገኛና የኢትዮጵያ ታሪክ፣ ባህል እና ስልጣኔን ከሚያንጸባርቁ ከተሞች መካከል አንዷ ናት።
ሆኖም በመጓጓዣ መሰረተ ልማቶች ምክንያት ከዘርፉ መጠቀም ያለባትን ያህል ሳትጠቀም መቆየቷን ገልፀዉ እነዚህ እምቅ ሀብቶች ሙሉ በሙሉ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም እንዲያመጡ የአየር ትራንስፖርት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
በዓለም ላይ የቱሪዝም ስኬት ያስመዘገቡ አገራት በቱሪስቶች ቀላል ተደራሽነት ላይ ትልቅ ትኩረት ሰጥተዋል።
ሀረር በተለይም በቱሪዝም ዘርፍ እምቅ አቅም እንዳላት የጠቆሙት አቶ ሔኖክ የአየር ማረፊያው ሲገነባ የውጭና የአገር ውስጥ ጎብኚዎች በአጭር ጊዜ ወደ ከተማዋ እንዲደርሱ ያስችላል።
ይህም የጎብኚዎችን የቆይታ ጊዜ ከማራዘም ባሻገር የሆቴል ኢንዱስትሪን፣ የባህል ማዕከላትን፣ የእጅ ሥራ ውጤቶችን እና አካባቢያዊ ንግዶችን ያነቃቃል ነው ያሉት።
ፕሮጀክቱ በሚገነባበት አካባቢ ለማገኘው ማህበረሰብም የስራ እድል ተጠቃሚነትን በማሳደግ ባለፈ መሰረተ ልማትን በማስፋፋት ረገድ ያለው ጠቀሜታ የጎላ መሆኑን ተናግረዋል።
በተጨማሪም ለወጣቶች በቱሪዝም፣ በሆቴል፣ በሎጂስቲክስ፣ በትራንስፖርት እና በሌሎች አገልግሎቶች ዘርፎች ላይ የሥራ ዕድሎች እንዲጎለብቱ ያደርጋል ብለዋል።
ስለሆነም የአየር ማረፊያ በክልሉ መገንባቱ የአየር ትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ብቻ ሳይሆን የቱሪዝም እምቅ አቅምን ወደ ተጨባጭ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም የሚቀይር፣ የሥራ ዕድል የሚፈጥር፣ የንግድና የኢንቨስትመንት ፍሰትን የሚያሳድግ እና ሀረር በምሥራቅ ኢትዮጵያ የቱሪዝምና የኢኮኖሚ ማዕከል እንድትሆን የሚያስችል ስትራቴጂያዊ እርምጃ መሆኑን ገልፀዋል።
10/07/2026
10/07/2026
በሀረሪ ክልል የንግድ አሰራርን ዘመናዊ በማድረግና ገበያን በማረጋጋት ውጤታማ ስራ መከናወኑ ተገለጸ
በሀረሪ ክልል የኢንተርፕራይዝ ልማት እና ኢንዱስትሪ ቢሮ በ2018 በጀት ዓመት አሰራርን ሙሉ በሙሉ ወደ ዲጂታል (ኦንላይን) ስርዓት በማሸጋገር፣ ህገ-ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎችን በመቆጣጠር እና የገበያ እንዲረጋጋ በማገዝ ረገድ አበረታች ውጤቶች መመዝገቡን አስታወቀ።
የቢሮው ኃላፊ አቶ እስማኤል ዩሱፍ እንደገለጹት፤ ክልሉ የንግድ ምዝገባና ፍቃድ አሰጣጥ አገልግሎትን ዘመናዊ በማድረግ ተገልጋዮች በቤታቸው ሆነው አገልግሎቱን እንዲያገኙ ማድረግ ተችሏል።
በዚህም መሰረት በበጀት ዓመቱ ለ19ሺህ 600 ነጋዴዎች ኦንላይን አገልግሎት ለመስጠት ታቅዶ ለ20ሺህ 265 ነጋዴዎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ጠቁመው በዚህም 6 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ጠቅሰዋል።
በንግድ ስርዓቱ ላይ እየታዩ ያሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በተከናወነው የክትትልና ቁጥጥር ስራም በ19 ሺህ 745 ድርጅቶች ላይ የድህረ-ፍቃድ ኢንስፔክሽን መደረጉን አብራርተዋል።
ከህግና ከመመሪያ ውጪ ሲነግዱ በተገኙ 1ሺህ 914 ነጋዴዎች ላይም አስተማሪ እርምጃ መወሰዱን ኃላፊው አስረድተዋል።
በተለይም በነዳጅ አቅርቦትና ስርጭት ዙሪያ በተወሰደው ጥብቅ ቁጥጥር በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረን 12 ሺህ 577 ሊትር መያዙን ተናግረዋል።
በተጨማሪም በህገ-ወጥ የነዳጅ ንግድ ላይ የተሰማሩ 49 ግለሰቦችና 12 ተሽከርካሪዎች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ጠቅሰዋል።
የክልሉ መንግስት በቀጣይ በጀት ዓመት የንግድ ዘርፉን የበለጠ በማዘመንና ህገ-ወጥ የንግድ አሰራሮችን በመከላከል የተረጋጋ ገበያ ለመፍጠር የተቀናጀ ስራ እንደሚሰራ ኃላፊው አረጋግጠዋል።
02/07/2026
በሀረሪ ክልል ሁለተኛው ዙር የ12ተኛ ክፍል ፈተና በነገው እለት መሰጠት ይጀምራል
ሀረር ፣ሰኔ 25/2018(ሀክመኮ):-በሀረሪ ክልል ሁለተኛውን ዙር የ12ተኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በነገው ዕለት መሰጠት እንደሚጀምር የክልሉ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።
በነገው ዕለት በሚጀመረው ፈተና በሀረሪ ክልል 2 ሺህ 678 ተማሪዎች ፈተናውን እንደሚወስዱ በመጠቆም ለፈተናው አስር የመፈተኛ ጣቢያዎች መዘጋጀታቸውንም የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጌቱ ነገዎ ገልፀዋል።
በፈተናው ወቅት የኔትወርክ እና የመብራት መቆራረጥ ችግሮች እንዳይከሰቱ ከወዲሁ ከኢትዮ ቴሌኮምና የመብራት ሃይል አገልግሎት ጋር በጋራ በመሆን ዝግጅት መደረጉንም አክለዋል።
በዚህም የኔትወርክና የመብራት መስመር ዝርጋታዎችን ጨምሮ ጀነሬተሮችና ሌሎች አስፈላጊ ዝግጅቶች መደረጋቸውንም ጠቁመዋል።
በሌላ በኩል ቢሮው የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የማጠናከሪያ ትምህርት ከመስጠት ጀምሮ ተማሪዎችን በስነልቦና የማዘጋጀት ስራ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Harar
NANII
Alerts
Be the first to know and let us send you an email when FiiRii Michael posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.
