Gobba sidaama ityophiya

Gobba sidaama ityophiya

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Gobba sidaama ityophiya, Health/Beauty, Hawassa.

14/01/2026

በወንጀል ክርክር በክስ አቀራረብ ሂደት የሚታዩ ችግሮች
➖➖➖➖➖➖➖➖➖➖
በአገራችን የወንጀል የፍትህ ሥርዓት ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛ ሚና ስልጣን ያለው አካል ነው፡፡ ዐቃቤ ህግ ሚናውን በአግባቡ መወጣት የወንጀል የፍትህ ሥርዓቱ ውጤታማነት ወሣኝነት አለው፡፡ በመሆኑም በክስ አቀራረብ ሂደት

📌ተከሣሹን በሀላፊነት የማያስጠይቁ እና የማያስቀጡ ሁኔታዎች መኖራቸውን ከምርመራ መዝገቡ በተያያዙት ማስረጃዎች ማለትም ተከሣሽ ለድርጊቱ ፍፁም ኢ ሀላፊ መሆኑን ፍፁም በሆነ መገደድ የፈፀመው መሆኑን አስገዳጅ በሆነ ሁኔታ ወይም በሕጋዊ መከላከያ የፈፀመው መሆኑን የሚያሣይ በቂ ማስረጃ እያለው ክስ የሚያቀርብበት ሁኔታ መኖሩ በቀዳሚነት የሚጠቀሰው ሲሆን ፣

📌ለዚህም መነሻው የወንጀለኛ መቅጫ ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 42/1/ሀ/ በእንደዚህ አይነት ምክንያቶች ዐቃቤ ሕግ ክስ አያስቀርብም ብሎ ለመወሰን ስልጣን አይሰጠውም የሚል ነው፡፡ ሆኖም የህጉን ድንጋጌ ስንመለከተው “ክስ ለማቅረብ የማይቻለው ጥፋተኛ ለማድረግ በቂ የሆነ መረጃ የሌለ መሆኑን ዐቃቤ ሕግ የተረዳ እንደሆነ” የሚል ሆኖ እናገኘዋለን፡፡
📌በመሆኑም የተሰበሰበው መረጃ ተከሣሹ በህጋዊ መከላከል ድርጊቱን መፈፀሙን የሚያስረዳ በሆነበት ሁኔታ ዐቃቤ ሕጉ ተከሣሹን ከስሶ ጥፋተኛ ለማድረግ የሚያስችል በቂ ማስረጃ አለው ለማለት ይቻላል?
📌ተከሣሹ የፈፀመው ድርጊት በሀላፊነት የማያስጠይቀውና የማያስቀጣው ሁኔታ መኖሩን በተሰበሰበው ማስረጃ ተረጋግጦ እያለ ዐቃቤ ህግ ዝም ብሎ ክስ ማቅረቡ ምን ጠቀሜታና ፋይዳ ይኖረዋልን የሚሉት ነጥቦች አገራዊ ችግር በመሆናቸው በውል መታየትና አስራሩ መስተካከል ይኖርበታል፡፡
📌በሁለተኛ ደረጃ ዐቃቤ ህግ በክስ አቀራረብ ላይ የሚስተዋለው ችግር ዐቃቤ ሕግ ክስ ለማቅረብ የሚያስፈልገው የማስረጃ እና ተከሣሹን ለማስቀጣት የሚያስፈልገው ማስረጃ ደረጃ /Standard of proof/ የተለያየ አድርጎ ማሰብ በደካማ ማስረጃ ክስ የሚመሰረትበት ሁኔታ መኖሩ ነው፡፡ በመሠረቱ የወንጀል ክስ ማቅረብ ብቻ በራሱ ግብ አይደለም፡፡ ስለሆነም ዐቃቤ ህግ ክስ ለማቅረብ በእጁ ያለው ማስረጃ በመጀመሪያ ተከሣሹን የሚያቀርባቸውን መከላከያ ማስረጃዎች የሚቋቋምና ተከሣሹን ጥፋተኛ ለማድረግ የሚችል መሆኑን በአግባቡ መመዘንና መመርመር ይኖርባቸዋል፡፡
📌ዐቃቤ ህግ ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ፣ እና ቦታ በድርጊት እና በውጤት መካከል ምክንያታዊ ግንኙነት መኖሩን አለማረጋገጥ፡፡ በዚህ ምክንያት ያልተሟላ ክስ የሚቀርብበት ሁኔታ ያለ መሆኑና በሌላ በኩል ወንጀሉ የተፈፀመበት ጊዜ የሚለው አባባል ፍርድ ቤት ጠብቦ የመተርጎም ችግር መኖር ለምሣሌ አንድ ገንዘብ ያዥ ከመስከረም2014 እስከ ሰኔ 2014 ከተቀበለው ገንዘብ ውስጥ 5ዐ,ዐዐዐ አጉድላለች የሚል ክስ ሲቀርብ 5ዐ,ዐዐዐ ብሩን በየትኛው ቀንና ወር እንዳጎደለች ገልፃችሁ ክሶችን ካላሻሻላችሁ እንቀበልም የሚባልበት አጋጣሚ መኖሩ በውል መታየትና መስተካከል ይገባዋል፡፡
📌ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ክስ ሲቀርብ ክሱን በአንድ ላይ ለማቅረብ የሚያስችል ምክንያት መኖሩን አለማረጋገጥ፣ ከአንድ በላይ የሆኑ ሰዎች ሊከሰሱ በወንጀሉ ያላቸውን የተሣትፎ ደረጃ በክሱ ውስጥ በአግባቡ ያለመግለፅ ከአንድ በላይ ወንጀል በተፈፀመ ጊዜ እያንዳንዱ የወንጀል ድርጊት ላይ ክስ አለማቅረብ ችግሮች ይስተዋላሉ፡፡ /የወ/መ/ሥ/ሥ/ሕ/ቁ.117/ ያላሟላ

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in Hawassa?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Hawassa