Sami Mentamo
Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from Sami Mentamo, Health/Beauty, Hosanna.
25/08/2026
ጭንቀት እና ምግብ ያላቸው ትስስር ምንድን ነው? ስንጨነቅ አመጋገባችን ይለወጣል?
ጭንቀት ጤና ያቃውሳል። ራስ ምታት፣ የሆድ ሕመም፣ እንቅልፍ ማጣት ያስከትላል። አመጋገብንም ያዛባል።
ስንጨነቅ ቸኮሌት ወይም ፒዛ ያምረናል። ለመሆኑ ጭንቀት አመጋገባችንን የሚለውጠው እንዴት ነው?
ጭንቀት ምንድን ነው?
የሥነ ልቦና ባለሙያ እና በዬል ዩኒቨርስቲ የጭንቀት ጥናት ምርምር ማዕከል የከፈቱት ፕ/ር ራጂታ ሳናሀ እንደሚሉት፤ ጭንቀት ማለት ሰውነት እና አእምሮ ለፈታኝ የሚሰጡት ምላሽ ነው።
"ምንም ማድረግ የምንችለው ነገር እንደሌለ ሲሰማን የሚመጣ ስሜት ነው" ይላሉ።
በአካባቢያችን የሚፈጠር ነገር ወይም አእምሯችን ውስጥ የሚፈጠር የስሜት መዋዠቅ አልያም ደግሞ እንደ ረሃብ እና ጥማት ያለ የሰውነት ለውጥ በአእምሯችን ውስጥ የሚገኘውን ሀይፖታላሙስ (hypothalamus) ላይ ለውጥ ያስከትላል። ይህ ለውጥ ነው ጭንቀት የሚያስከትለው።
ባለሙያዋ እንደሚሉት፤ ይህ የሰውነታችን ክፍል ምላሽ የሚሰጠው እንደ አድረነሊን እና ኮሪስትሮል ያሉ ሆርሞኖች ለውጥ ሲፈጠር እንዲሁም የልብ ምት እና የደም ዝውውር ሲቀየር ነው።
ለአጭር ጊዜ የሚቆይ ጭንቀትን ሰውነት ራሱን ከአደጋ እንዲከላከል ስለሚያነቃቃ እምብዛም አይጎዳም።
ሆኖም ግን ዘለግ ላለ ጊዜ የሚቆይ ጽኑ ጭንቀት (chronic stress) የጤና ቀውስ ያስከትላል።
24/08/2026
ሆርሙዝ ወሽመጥ በመስተጓጎሉ የኃያላን የፍጥጫ ማዕከል የሆነው ፓናማ ካናል
,ፓናላ ካናል ከዓለም የባህር ንግድ የሚያስተላልፈው 5 በመቶ ገደማ ነው፤ ከአሜሪካ ጭነት ውስጥ ግን 40% ገደማው ይጓጓዝበታል
የኢራን ጦርነት ከዓለም ወሳኝ የባሕር መስመሮች አንዱ የሆነውን የሆርሙዝ ወሽመጥ መተላለፊያነት ባስተጓጎለበት በዚህ ወቅት፣ በሺህ ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኝ ሌላ የባሕር መስመር ውጥረት ምንጭ ሆኖ ብቅ ብሏል። ይህ የባሕር መስመር አትላንቲክ እና ፓሲፊክ ውቅያኖሶችን የሚያገናኘው የፓናማ ካናል ነው።
አሜሪካ በካናሉ ላይ እየጨመረ የመጣው የቻይና ተፅዕኖ፣ ዓለም አቀፍ ንግድ እና ደኅንነትን አደጋ ላይ ይጥላል በሚል አስጠንቅቃለች።
ክሱን ውድቅ የምታደርገው ቻይና በበኩሏ፣ አሜሪካ ይህንን ጉዳይ በውሃ መስመሩ ላይ ያላትን ቁጥጥር ለማስፋፋት እንደ ምክንያት እየተጠቀመች ነው የሚል ወቀሳ አቅርባለች።
በሁለቱ ኃያላን መሃል የገባችው ፓናማ ደግሞ በካናሉ ላይ ሉዓላዊነቷ የተጠበቀ መሆኑ እንዲሁም በውዝግቡ ላይ ገለልተኛ ሆና እንደምትቀጥል ገልጻለች።
የምስሉ መግለጫ,ካናሉ መርከቦችን ከባህር ወለል በላይ ወደ ጋቱን ሐይቅ ለማንሳት እና ተቃራኒው አቅጣጫ ወደሚገኘው የባህር ዳርቻ ለማሳረፍ የሚያስችል ውሃን ከፍ እና ዝቅ የሚያደርግ (ሎክስ) ሥርዓት ይጠቀማል
ፓናማ ካናል በፓናማ ልሳነ ምድር የተዘረጋ እንዲሁም አትላንቲክ እና ፓሲፊክ ውቅያኖሶችን የሚያገናኝ የ80 ኪሎ ሜትር ሰው ሠራሽ የባሕር መተላለፊያ ነው።
ካናሉ፤ መርከቦች በደቡብ አሜሪካ ደቡባዊ ጫፍ የሚገኘውን ኬፕ ሆርን በመዞር የሚያደርጉት ረጅም ጉዞ እንዲቀንስ ያደርጋል። የባሕር መተላለፊያው መኖር፣ ጉዞው የሚወስደውን ጊዜ እና የትራንስፖርት ወጪን በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል።
በካናሉ የሚያልፉ መርከቦች የትራንዚት ክፍያ ይከፍላሉ። ክፍያው የሚወሰነው እንደ የመርከቡ መጠን እና ዓይነት እንዲሁም ጭነት ያሉ ሁኔታዎች ከግምት ውስጥ ገብተው ነው።
ካናሉ መርከቦችን ከባሕር ወለል በላይ ወደ ጋቱን ሐይቅ ለማንሳት እና ተቃራኒው አቅጣጫ ወደሚገኘው የባሕር ዳርቻ ለማሳረፍ የሚያስችል ውሃን ከፍ እና ዝቅ የሚያደርግ (ሎክስ) ሥርዓት ይጠቀማል።
24/08/2026
በኬንያ ሺዎችን ለማዕድን ፍለጋ ያራኮተው አንድ የፍየል እረኛ ያገኘው ትንሽ ወርቅ
የምዕራብ ኬንያ ነዋሪ የሆነ አንድ የፍየል ጠባቂ ያገኘው ትንሽ ወርቅ ማኅበረሰቡ ለወርቅ ፍለጋ እንዲራኮት ማድረጉን ለቢቢሲ ተናገረ።
የ33 ዓመቱ ማናሴ ሎማቻር እንደሚለው የአካባቢው ነዋሪዎች በገጠራማዋ ትንሽ መንደር ወርቅ ለመፈለግ የተሰማሩት ከበርካታ ሳምንታት በፊት ያገኛትን ሦስት ግራም ወርቅ በ280 ዶላር መሸጡ ከተሰማ በኋላ ነው።
ይህንንም ተከትሎ ከአንድ ወር በፊት በቸፖሮር መንደር አቅራቢያ ጥሻ እና የግጦሽ ሥፍራ የነበረው መሬት አሁን ላይ በጉድጓድ፣ በአፈር ቁልል እንዲሁም በማዕድን ማውጫ ካምፖች ተወርሷል።
በእርግጥ ይህንን የፈጠረው የሎማቻር ዕድል ይሁን ሌሎች የቅርብ ጊዜ ግኝቶች ግልፅ አይደለም።
ሆኖም የአካባቢው ባለሥልጣናት ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች በአካባቢው ለወርቅ ፍለጋ መሰማራታቸውን ገልጸዋል።
ውድ የሆነው ማዕድን በአብዛኛው ኑሯቸው በግብርና ላይ የተሰመረተ የኡጋንዳ እና የኬንያ ሰዎችን ሕይወት ይለውጣል። ሆኖም ሰዎች በአካባቢው ወርቅ ለመግኘት ቢቆፍሩም እስካሁን እዚህ ግባ የሚባል ነገር አላገኙም።
የፍየል እረኛው ሎማቻር እንደሚለው ወርቅ ያገኘው የጠፋችበትን ፍየል ሲፈልግ በአጋጣሚ ነው። በወንዙ አቅራቢያ ሴቶች ወርቅ ሲፈልጉ እንደተመለከተ እና እንደተቀላቀላቸው የሚናገረው ሎማቸር፣ ትንሽ ወርቅ ካገኘ በኋላ መንደርተኛው በአካባቢው ወርቅ እንዳለ መገንዘቡን ያስረዳል።
የምዕራብ ፖኮት አውራጃ ምክትል ኮሚሽነር ሳሙዔል ኬሬ እንደሚሉትም መራኮቱ የጀመረው ሁለት ጊዜ ወርቅ መገኘቱን ተከትሎ ነው።
24/08/2026
23/08/2026
በፊትቦትስዋና የሩሲያን ጦር ለመቀላቀል በሚሞክሩ ዜጎቿ የተነሳ ስጋት እንዳደረባት አስታወቀች
ቦትሰዋና የሩሲያን ጦር ለመቀላቀል የሚሄዱ ስምንት ዜጎቿን ማስቆሟን የአገሪቱ ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር ፌንዮ ቡታሌ ተናገሩ።
ሚኒስትሩ አርብ ዕለት ለደቡብ አፍሪካ አገራት ፓርላማ "በሩሲያ እና በዩክሬን ግጭት ላይ እንዲሳተፉ የሚመለመሉ ወይም ለምልመላ ዒላማ የሚደረጉ የቦትስዋና ዜጎች ቁጥር መጨመሩ መንግሥትን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ጥሎታል።" ብለዋል።
"ዜጎቻችን በቅጥር፣ በሥልጠና ወይም በደኅንነት ሥራ ሽፋን በሚቀርቡ ማባበያዎች ተታለው፣ በጭራሽ አስበውት በማያውቁት የውጊያ ግንባር እንዲሰለፉ ስለመደረጋቸው የሚያሳስቡ ሪፖርቶች እየደረሱን ነው።" ሲሉ አክለዋል።
ቡታሌ "እስካሁን ድረስ ወደ 22 የሚጠጉ የቦትስዋና ዜጎች በእነዚህ አማላይ የቅጥር ማባበያዎች ተታልለው ሄደዋል" ብለዋል።
"ከወዳጅ አገራት ጋር በመሆን ባደረግነው ጥብቅ ክትትልና የቅርብ ትብብር፣ በሰር ሴሬትሴ ካማ፣ በኦአር ታምቦ እና በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያዎች ጉዟቸውን ለመጀመር በተቃረቡበት ወቅት፣ ወደ ጦርነት ውስጥ ከመግባታቸው ጥቂት ቀደም ብለን፣ ስምንት ግለሰቦችን ማስቆምና መመለስ ችለናል።" ሲሉ አክለው ገልጸዋል።
ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አታላይ በሆኑ የሰዎች ዝውውር መስመሮች አማካኝነት በሺዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን ወደ ሩሲያ ጦር ሠራዊት እንዲቀላቀሉ መደረጉ ከፍተኛ ቁጣንና ዲፕሎማሲያዊ ውጥረትን አስከትሏል።
20/08/2026
በፊትሩሲያ በዩክሬን ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 13 ሰዎች ተገደሉ
ሩሲያ በዩክሬን መዲና ኪቭ ላይ ባደረሰችው ጥቃት ቢያንስ 13 ሰዎች ተገደሉ።
የዩክሬን ጠቅላይ ሚኒስትር እንደተናገሩት ተጨማሪ 40 ሰዎች ጉዳት ደርሶባቸዋል።
የዩክሬን መዲና የአየር መቃወሚያ ሚሳዔል እጥረት እንደገጠማትም ገልጸዋል።
የአገሪቱ የድንገተኛ ጊዜ መሥሪያ ቤት እንዳለው፤ ትናንት ምሽት በመኖሪያ ሕንጻዎች እንዲሁም መጋዘን ላይ ጥቃቶች ተፈጽመዋል። በተጨማሪም የሕጻናት ሆስፒታል እና ትምህርት ቤቶች ተጎድተዋል።
የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ እንደተናገሩት ከሆነ ሰዎች የተገደሉት የአየር መቃወሚያ ሚሳዔል እጥረት በመከሰቱ ነው።
ዩክሬን የአየር መቃወሚያ ሚሳዔል የምታገኘው ከምዕራባውያን አገራት ነው።
የቪቭ ከንቲባ ቪታሊ ክሊትሽኮ “የአየር መቃወሚያ ሚሳዔል እና የተተኳሾች ድጋፍ እንፈልጋለን” ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ከሕንጻ ፍርስራሾች ሥር በሕይወት የተረፉ ሰዎችን ለማግኘት እየሞከሩ ነው።
18/08/2026
“ትራምፕ ስለ ሆርሙዝ ወሽመጥ ያላቸውን ቅዠት በቅርቡ እናስተካክለዋለን”- ኢራን
ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝ ወሽመጥን “አዲስ የአሜሪካ ግዛት” ማለታቸውን ተከትሎ የኢራን የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትር ካዚም ጋሪባባዲ “ቅዠታም” ሲሉ ፕሬዝዳንቱን ወርፈዋል።
“ዶናልድ ትራምፕ የፐርዥያ ባሕረ ሰላጤን በትክክል መጻፍ እንደተማሩት ሁሉ ስለ ሆርሙዝ ወሽመጥ ያላቸውን ቅዠትም በቅርቡ እናስተካክለዋለን” ሲሉ ጽፈዋል።
ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል ማኅበራዊ ሚዲያቸው በለጠፉት ምሥል ላይ የሆርሙዝ ወሽመጥን አክብበው “የአሜሪካ አዲስ ግዛት” ሲሉ ጽፈዋል።
የኢራኑ የውጭ ጉዳይ ምክትል ሚኒስትርም ይሄንን ምሥል በድጋሚ አጋርተዋል።
በሌላ በኩል የኢራን ፓርላማ አፈ ጉባዔ መሐመድ ባጋር ጋሊባፍ በበኩላቸው አሜሪካ የመግባቢያ ሰነዱን ስምምነቶች ካልተገበረች የሆርሙዝ ወሽመጥ እንደማይከፈት አስታውቀዋል።
15/08/2026
በኢንዶኔዢያ በተከሰተ ከባድ ርዕደ መሬት ቢያንስ 38 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቷ የአደጋ መከላከያ ድርጅት ገለጸ። ቅዳሜ ዕለት በፍሎርስ ግዛት የተከሰተው ርዕደ መሬቱ በሬክተር ስኬል 7.7 ማግኒቲዩድ የተለካ ነው።
15/08/2026
ቅዳሜ ዕለት በኢራን የሚደገፉት ሁቲዎች በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እውቅና ያለው መንግሥት የሚቆጣጠረውን የቀይ ባሕር ወደብ ማጥቃታቸውን እና አንድ የደኅንነት አባል መግደላቸውን የየመን ጦር ገለጸ። የጦሩ ቃል አቀባይ ኮሎኔል ማጂድ አል ናዚሊ በሰጡት መግለጫ አርብ ምሽት ሁቲዎች ወደ ሞቻ ወደብ ስድስት ባሊስቲክ ሚሳዔሎች መተኮሳቸውን ተናግረዋል።
Click here to claim your Sponsored Listing.
Category
Contact the business
Telephone
Website
Address
Hosanna
