FiFi

FiFi

Share

Contact information, map and directions, contact form, opening hours, services, ratings, photos, videos and announcements from FiFi, Health/Beauty, newyork, New York, NY.

09/14/2026

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ፕሬዚዳንት ፑቲን አንድ ላይ ተጉዘው ወደ ስብሰባ ሲገቡ

Prime Minister Abiy Ahmed and President Vladimir Putin travel together to a meeting in New Delhi

Photos from FiFi's post 09/02/2026

በፍፁም ተቀባይነት የሌለው አሳፋሪ ድርጊት ነው!!

በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ የተስተዋለውና አንድ አሽከርካሪ የትራፊክ ደንብ በመጣሱ ምክንያት ቅጣት ሲጣልበት ከትራፊክ ተቆጣጣሪዎች ጋር ወደ አካላዊ ግጭትና ድብድብ ሲገባ የሚያሳየው ምስል እጅግ አሳፋሪ ነው።

ህግ አስከባሪዎች የራሳቸውን የግል ፍላጎት ሳይሆን የሀገርንና የህዝብን ደህንነት ለማስጠበቅ በስፍራው የተገኙ የመንግስት እና የህዝብ ወኪሎች ናቸው። እነሱን መንካት፣ መሳደብ ወይም መደብደብ ቀጥታ ህግንና ስርዓትን እንደመደብደብ፣ እንዲሁም የህዝብን ደህንነት አደጋ ላይ እንደመጣል ይቆጠራል።

በዚህ ድርጊት ዙሪያ የሚነሱ ክርክሮች አብዛኛውን ጊዜ የሚያተኩሩት "ቅጣቱ በዛ" ወይም "ለምን ታርጋ ይፈታል" በሚሉ የቅጣት አፈጻጸም ጉዳዮች ላይ ነው። ነገር ግን ትልቁና መሰረታዊው ጥያቄ መሆን ያለበት፣ "አሽከርካሪው ገና ከመነሻው ለምን የትራፊክ ህግን ጥሶ ተገኘ?" የሚለው ነው።

የትራፊክ ህጎች የተነደፉት የዜጎችን ውድ ህይወት ለመታደግ እና የሀገርን ሀብት ከውድመት ለመጠበቅ ነው። የትራፊክ አደጋ በሰው አካል፣ ህይወት እና በንብረት ላይ የሚያደርሰው ዘግናኝ ጉዳት በቀላሉ የሚታይ አይደለም፤ ስንት ቤተሰብን በትኗል፣ ስንቱን አካል ጉዳተኛ አድርጓል። ይህንን እልቂት ለማስቆም፣ ስርዓት እንዲከበርና አደጋዎች እንዲቀንሱ ከተፈለገ፣ ህግን መተላለፍ የሚያስከትለው ዋጋ እጅግ ከባድ ሊሆን ይገባል።

ያደጉትን ሀገራት ተሞክሮ ብንመለከት፣ ለምሳሌ በአሜሪካ የትራፊክ ህግን መተላለፍ የሚያስከትለው የገንዘብ ቅጣት እጅግ በጣም ከፍተኛ እና አንዳንዴም የመንጃ ፈቃድን እስከማሳጣት የሚያደርስ ነው። ከቅጣቱ ክብደት የተነሳ አሽከርካሪዎች ከፍተኛ ጥንቃቄ ያደርጋሉ፤ ህግን ላለመጣስም ይጥራሉ።

ወደ እኛ ሀገር ስንመጣ ግን "ትንሽ ተሳሳቱ፣ ስለዚህ ትንሽ ይቀጡ" የሚል የተሳሳተ አመለካከት ይስተዋላል። በሰው ህይወት ላይ የሚቀለድበት "ትንሽ ጥፋት" የለም፤ ምክንያቱም አንዲት ትንሽ የምትመስል የትኩረት ማጣት ወይም የህግ ጥሰት የብዙዎችን ህይወት በሰከንዶች ውስጥ ልትቀጥፍ ትችላለችና። ህግ ህግ ነው፤ ጥፋት ከተፈጸመ ተመጣጣኝ እና ዳግም እንዳይደገም የሚያደርግ አስተማሪ ቅጣት ሊኖር ግድ ይላል።

አንድ ግለሰብ የራሱን ጥፋት ለመሸፈን፣ ወይም ከቅጣት ለማምለጥ ብሎ የህግ አስከባሪዎችን በጉልበት ለማሸነፍ መሞከሩ ፍጹም አጸያፊና ስርአት አልበኝነት ነው።

ይህ ዓይነቱ ድርጊት ማህበረሰባዊ ቀውስን የሚጋብዝ እና በምንም ዓይነት መለኪያ ተቀባይነት የሌለው ተግባር ነው።

የህግ አካላት ስራቸውን በአግባቡ ሲሰሩ ሊደገፉና ሊበረታቱ እንጂ፣ በአደባባይ ጥቃት ሊሰነዘርባቸው አይገባም። ማንኛውም ዜጋ ቅሬታ ካለው በሰለጠነና በህጋዊ መንገድ ማቅረብ ሲችል፣ አቋራጭ እና የጉልበት መንገድን መምረጥ ትልቅ ድንቁርና ነው።

ማህበረሰባችን ይህንን አሳፋሪ ድርጊት በጽኑ ሊያወግዘው እና የህግ የበላይነት ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲከበር በጋራ ሊቆም ይገባል። ህግን ማክበር የፍርሃት ሳይሆን የስልጣኔ እና የኃላፊነት ስሜት መገለጫ መሆኑን ተረድተን፣ ለህግ እና ህግን ለማስከበር ለቆሙ አካላት ተገቢውን ክብር መስጠት የሁላችንም የማይደራደር ግዴታ ነው።

08/24/2026
Photos from FiFi's post 08/17/2026

እንኳን ደስ አላችሁ!
እንኳን ደስ አለን!

ኮልፌ የጥረት እና የስኬት ተምሳሌት

የኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ኮሙኒኬሽን ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት ዓመት
በሰራቸው ስራዎች ከፍተኛ አፈፃፀም በማስመዝገብ የዋንጫ እና የምስክር ሰርተፍኬት የላቀ ተሸላሚ ሆነ።

Photos from FiFi's post 08/16/2026

እንኳን ደስ አለን!!

ዛሬ በከተማችን በቀን 60 ሺህ ሜትር ኪዮብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ የሚያመርት እና በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዮብ ፍሳሽ የሚያጣራ የኮዬ ፍሳሽ ዘመናዊ ማጣሪያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን አስመርቀን አገልግሎት አስጀምረናል።

ንጹህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትን ለማሳደግ በቱሉ ጉዶ፣ ለገዳዲ ክፍል 2፣ በረከት የጋራ መኖሪያ አካባቢ፣ ቦሌ አራብሳና ሌሎችም በርካታ ጉድጓዶችን አልምተን በከተማችን ከአምስት ዓመት በፊት የነበረው 525 ሺህ ሜትር ኪዩብ በቀን የማምረት አቅም ዛሬ ላይ 910 ሺህ ሜትር ኪዩብ አድርሰናል፡፡

በተመሳሳይ ለረጅም ዘመን በከተማችን የሚገኙ ወንዞች በፍሳሽም፤ በደረቅ ቆሻሻም ሲበከሉ ቆይተዋል። ይህንን ችግር ለመፍታት የፍሳሽ መሰረተ ልማትን ለማስፋፋትና የማጣራት አቅምን ለማሳደግ ከለውጡ ወዲህ ለዘርፉ በሰጠነው ከፍተኛ ትኩረት በ2009 ዓ .ም በቀን 20 ሺህ ሜትር ኪዩብ ብቻ የነበረው ፍሳሽ የማጣራት አቅማችን የዛሬውን ጨምሮ ከ253 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ ማሳደግ ችለናል፡፡

ፕሮጀክቶቹ የነዋሪዎቻችንን ጤናና ንጽህና የሚጠብቁ፣ የወንዞቻችንን ብክለት የሚቀንሱ፣ የአካባቢ ጥበቃችንን የሚያጠናክሩ ናቸው። አዲስ አበባን እንደ ስሟ አዲስ ውብ፣ ጽዱ፣ ጤናማ፣ አረንጓዴ፣ ዘመናዊና ለትውልድ የምትመች ከተማ ለማድረግ የጀመርነው ግብ ተጠናክሮ ይቀጥላል ።

ይህንን ታላቅ ፕሮጀክት እውን ላደረጋችሁ፤ በተለይ ደግሞ በተለያዩ ፕሮጀክቶች ላይ የብድር አገልግሎት እየሰጠን ያለውን የዓለም ባንክ፣ እንዲሁም የውሃው መገኛ አካባቢዎችን በትብብር እንድናለማ ላገዘን የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልል፣ ከሁሉ በላይ ዘላቂ ኑሯቸውን ሲመሩበት የነበረውን መሬት ለዚህ ታላቅ ልማት የለቀቁ አርሶ አደሮች እና ለፕሮጀክቱ ስኬት ሌት ተቀን ያለእረፍት የተጉ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን አመራሮች እና ባለሙያዎችን በራሴና በከተማ አስተዳደራችን ስም ከልብ አመሰግናለሁ!

ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ህዝቦቿን ይባርክ!
ከንቲባ አዳነች አቤቤ

07/21/2026

የአዲስ አበባ ለውጥ ኢትዮጵያ የዲፕሎማሲና የኮንፍረንስ ማዕከልነቷን ያደሰችበት ጉዞ ነው

ኢትዮጵያ ታሪካዊ የአፍሪካ መዲናነቷንና ዲፕሎማሲያዊ ገጽታዋን በአዲስ መልክ በመገንባት፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ተመራጭ የኮንፍረንስና የኤግዚቢሽን ማዕከል ለመሆን በቃች። ​በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ መሪነት ባለፉት ጥቂት ዓመታት የተከናወኑት ግዙፍ ፕሮጀክቶች አዲስ አበባን ለአለም አቀፍ ጉባኤዎች ይበልጥ ማራኪና ዝግጁ አድርገዋታል።

አድዋ ድል መታሰቢያ ግዙፍ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችንና ሁነቶችን ለማስተናገድ የሚያስችል ዘመናዊ የአዳራሽና ኤግዚቢሽን ማዕከል፣ የአፍሪካ ህብረት አዲስ አዳራሽና አቪዬሽን ከተማ፣ ግዙፍ አየር ማረፊያዎችንና መስተንግዶዎችን ጨምሮ የተከናወኑ የትራንስፖርትና የሎጅስቲክስ ማሻሻያዎች ይበልጥ ተመራጭ አድርጓታል። በተጨማሪም ወዳጅነት ፓርክ፣ የእንጦጦ ፓርክና የዓመታት የሸገር ውበት ፕሮጀክቶች ለአለም አቀፍ እንግዶች ምቹ፣ ጽዱ እና አረንጓዴ አካባቢን በመፍጠር የመዲናዋን ገጽታ ሙሉ በሙሉ ቀይረዋል።

Photos from Kolfe Keranio Communication /ኮልፌ ቀራኒዮ's post 06/24/2026
Photos from FiFi's post 06/22/2026

የሸገር ዳቦ ምርት ተደራሽነትን ማሻሻል ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ።

የኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የሸገር ዳቦ አቅራቢ ማህበራት ለማህበረሰቡ የሚያቀርቡትን ምርት በጥራትና በተደራሽነት ማቅረብ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄደ።

በውይይቱ ላይ ማህበራቱ የዳቦ ምርትን በአግባቡ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ማድረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ በስፋት የተመካከሩ ሲሆን ማህበራቱ የሚያነሷቸውን የመልካም አስተዳደር ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታትም የጋራ ምክክር ተደርጓል።

በተጨማሪም ማህበራቱ በስራ ሂደት ላይ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችል የጋራ ውይይት ተደርጓል።

ዉይይቱን የመሩት የክፍለ ከተማዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ቴዎድሮስ ወ/ሚካኤል የአቅርቦት ሰንሰለቱን ውጤታማ ለማድረግና የዳቦ ፍላጎት በአስተማማኝ ሁኔታ ለማሟላት የክፍለ ከተማው አስተዳደር አስፈላጊውን ድጋፍ ለማህበራቱ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታዉቀዋል።

Want your business to be the top-listed Beauty Salon in New York?
Click here to claim your Sponsored Listing.

Category

Website

Address


Newyork
New York, NY

Alerts

Be the first to know and let us send you an email when FiFi posts news and promotions. Your email address will not be used for any other purpose, and you can unsubscribe at any time.

Subscribe

We will notify you when anything happens in New York.